
በዩኒቨርሲቲው “Center for Volunteerism(የበጎ ፈቃድ ማዕከል)”እና የበጎ ፈቃደኞች እውቅና ፕሮግራም ተካሄደ::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ግንቦት02/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ “Center for Volunteerism/የበጎ ፈቃድ ማዕከል”እና የበጎ ፈቃደኞች እውቅና ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን: የክብር እንግዶች: እንዲሁም የማእከሉ መስራች አባል የሆኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እና ተማሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል::
በአቶ ሰይድ አህመድ (የሰይድ አህመድ ጠቅላላ ንግድ/ጅንዱ ፋሚሊ በጎ ፈቃድ ከ8.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተሰራ ደረጃውን የጠበቀ የተማሪዎች አረንጓዴ የመናፈሻ ቦታ ተመርቋል::

ለዚህም ዩኒቨርሲቲው ለአቶ ሰይድ አህመድ (የሰይድ አህመድ ጠቅላላ ንግድ/ጅንዱ ፋሚሊ የእውቅና እና የምስጋና ሰጥቷል::
በአቶ መሀመድ ሀሰን-ሮኪያ የምግብ ዝግጅትና መስተንግዶ እየተሰራ ያለውን በቅርቡ የሚመቀውን የአረንጓዴ ልማት እና የመዝናኛ ቦታ ምልከታ ተደርጓል::
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን አቶ ሰይድ እና አቶ መሀመድ በግቢ ውስጥ ለተማሪዎች ምቹ ቦታን ለመፍጠር እየሰሩት ያለው የመዝናኛ ቦታ ልማት እጅግ በጎ አድራጊነትን የተላበሰ: ሁሉም በአርዓያነት ሊወስደው የሚገባው መሆኑን በማመስገን ገልጸዋል::
“Center for Volunteerism” በዩኒቨርሲቲው መመስረቱ ሁሉም ሰው ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንድወጣ መደላድል የሚፈጥር ሲሆን ፣ ተቋማዊ ግቦች እንድሳኩ፣ የማህበረሰብ ፍላጎቶች እንድፈቱ እና የተማሪ እና የሰራተኞችን አስተዋፅዖ የማበርከት ባህልን እንድያዳብሩ የሚያግዝ መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚሁ መድረክ “የሰመራ ዩኒቨርሲቲ “Center for Volunteerism” ዳይሬክተር ሆነው ሀላፊነት የተሰጣቸው ዶ/ር ኢፋ ታደሰ ደበሌ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል:: በተጨማሪም የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን ዶ/ር አጥናፉ ረጋሳም በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎችን የተመለከተ ፅሁፍ አቅርበዋል::
መድረኩ በርካቶች የ Center for Volunteerism አላማን በመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጾ ለማበርከት ቃል የገቡበት ነበር::
መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ