
ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
መስከረም 05/2018_ሠዩ_ህ/ግ/ስ/አስፈጻሚ-ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከ 200 በላይ ለሚሆኑ በገቢረሱ ዞን፣ ሀንሩካ ወረዳ ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የወረዳው አስተዳደር በተረከበበት ወቅት፣ ጊዜው የ2018 ትምህርት ዘመን የሚጀመርበት በመሆኑ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመውሰድ ቁሳቁስ ማሟላት ለሚከብዳቸው ወላጆች ወሳኝ እገዛ ነው ሲሉ አስተዳደሩ አቶ ሠዓድን ኡመር ገልጸዋል::
በተጨማሪም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ም ፕሬዚዳንት አቶ አደም አሊ እንደገለጹት ተማሪዎች በትምህርት ግብዓት እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ለማበረታታት ዩኒቨርሲቲው በየአመቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርገው ድጋፍ መሆኑን ገልጸው፣ትምህርት የብዙሃኑን ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በግልም በቡድንም እንደ ተቋምም ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ቢወጣ ሲሉ አክለዋል::
መንግስት ማንኛውም እድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅ ትምህርት ቤት መሄድ እንዳለበት በተደጋጋሚ እየገለፀ ይገኛል ፣ ስለሆነም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ እንድወስዱ ስንል መልእክት እናስተላልፋለን::
