
ፕሬዚደንቱ በዩኒቨርሲቲው የዶ/ር ሬዶ የባህል እና ሀገር በቀል ጥናቶች ማዕከልን ጎበኙ::
#ሰመራዩኒቨርሲቲ_ታህሳስ23_2018ዓም-የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ ከፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ፣ እንድሁም የአፋር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሙሣ አብዱ፣ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር ሬዶ የባህል እና ሀገር በቀል ጥናቶች ማዕከልን ጎብኝተዋል::

ፕሬዚደንቱ ጉብኝቱን ያደረጉት፣ ለይፋዊ የስራ ጉዳይ በአፋር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በተገኙበት ወቅት ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው በማዕከሉ የአፋርን ባህል እና ሀገር በቀል እውቀቶች ማጥናት፣መጠበቅ እና ማስተዋወቅ ላይ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን ጎብኝተው አድናቆታቸውን ገልፀዋል። ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ላደረጉት ጉብኝት እና ለሰጡት ገንቢ አስተያየት ያመሰግናል።