ተመራቂ የጤና ተማሪዎች ለአንድ ወር ያካሄዱት ነፃ የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት Team Training Program በደም ልገሳ  ፍፃሜዉን አግኝቷል። 

ተመራቂ የጤና ተማሪዎች ለአንድ ወር ያካሄዱት ነፃ የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት Team Training Program በደም ልገሳ  ፍፃሜዉን አግኝቷል። 

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ታህሳስ_24_2018ዓም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የ Team Training Program (TTP)፣ በሎጊያ ፣ በዱብቲ ፣በሰመራ ከተማ እና በዩኒቨርሲቲው ዉስጥ ለ አንድ ወር ያህል ሲያከናውኑት የነበረው  የማህበረሰብ ጤና አገልግቶች ስራ ዛሬ የደም ልገሳ መርሃግብር በማድረግ ፍፃሜዉን አግኝቷል።  

በዚህ መርሃግብር ኮሌጁ በአመቱ አጋማሽ በጥር ወር የሚያስመርቃቸው 200 የሚሆኑ የ Nursing, Public Health, Health Informatics, Midwifery ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች የተሳተፉበት ነው ተብሏል::

አገልግሎቱ የተከናወነው ከጤና ጋር ተያያዥ የሆኑ፣ ሰዎችን ለበሽታ ሊያጋልጡ የሚችሉ ችግሮች ያሉባቸውን ቦታዎች በመለየት፣ በራስ አቅም፣ ድጋፍ በማሰባሰብ፣ ማህበረሰቡን በማስተባበር የተከናወነ ሲሆን፣ በተማሪዎች ካፌ ከንፁህ መጠጥ ዉሃ እና የመመገቢያ ሳህን መደራደሪያ እንድሁም የሰራተኞች ንፅህና አጠባበቅን የሚያሻሽሉ አገልግሎቶችን ሰጥተዋል::

በዩኒቨርሲቲው ዉስጥ ለሚገኙ ስድስት የቢዝነስ ሴንተሮች የእጅ መታጠቢያ ጀሪካኖችን አበርክተናል፣ በግቢ ውስጥ ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች የደረቅ ቆሻሻ መጣያ አስቀምጠናል እንዲሁም ብዙሀኑን ያሳተፈ የፅዳት ዘመቻ አድርገናል ሲል የTTP እስተባባሪ የሆነው ተማሪ ኢብራሂም ገልጿል። 

በተጨማሪም ከክልል ጤና ቢሮ በድጋፍ የተገኙ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ለተማሪዎች ክሊኒክ፣ የእጅ መታጠቢያ ሳሙናዎችን ለተማሪዎች መኝታ ብሎኮች አስረክበናል ሲል አስታውቋል::

በማሳረጊያ መርሃግብር ከክልል የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር 40 ሰው ደም ሊለግስ ችሏል ሲል ገልጿል::

የTTP ፕሮግራም ተማሪዎች በፅንሰ ሀሳብ  የተማሩትን ማህበረሰቡ ውስጥ በመግባት ነባራዊ  ችግሮችን በተግባር መፈታት፣ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ከአቅም በላይ የሚሆኑ ችግሮችን ለአመራሮች ሪፖርት የማድረግ፣በጋራ የመስራትን ተግባራዊ አቅም እንደፈጠረላቸው ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገልፀውልናል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *