
በክልሉ 10 ወረዳዎች ለ 500 ሰዎች ሲሰጥ የቆየው የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ::
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከGIZ-PSDE እና ከአፋር ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በ10 የክልሉ ወረዳዎች ለ250 የቢዝነስ ኢንተርፕራይዞች፣ 500 ሰልጣኞችን ያሳተፈ፣ ለ1 ወር ያክል በተለያዩ ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች ሲሰጥ የቆየው የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና የመጀመራ ዙር ማጠቃለያ በጭፍራ ከተማ ተካሂዷል::

በዚህ ስልጠና የተመረጡ ወረዳዎችና ከተማ አሰተዳደሮች አብዓላ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ፣ ሰመራ፣ ሎጊያ፣ ሚሌ፣ አይሳኢታ፣ በራህሌ እና ዱብቲ ሲሆኑ ከእያንዳንዱ ወረዳ 50 ሰልጣኞች ከ25 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተመረጡ ሲሆን፣ ከእያንዳንዳቸው ኢንተርፕራይዞች 2 ሰልጣኞችን በማሳተፍ ሁለገብ የንግድ ክህሎት ስልጠናውን ወስደዋል።

ይህ ፕሮጀክት ከ GIZ፣ ከኔዘርላንድስ መንግሥት እና ከአውሮፓ ኅብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን ኢኮኖሚ ማንሰራራት ለማገዝ፣ በሥራ ፈጠራ፣ በፋይናንስ እውቀት እና በንግድ ስራ አስተዳደር ዙሪያ እየተተገበረ ያለ ነው።

በተጨማሪም በቀጣይ እነዚህ ጥቃቅንና አነስተኛ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዞችን የሁለታኛ ዙር ስልጠና፣ የማማከር አገልግሎትና እና ከፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠርና በማገናኘት ከተቋማቱ ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ የሚያገኙበትን ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
