የዩኒቨርሲቲው ሴኔት እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ምርቃት እና የ 18 Applied Science ፕሮግራሞችን አጸደቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ምርቃት እና የ 18 Applied Science ፕሮግራሞችን አጸደቀ፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መጋቢት 10/2018 ባደረገው ስብሰባ በሁለት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::

ሴኔቱ የ2018ዓ.ም የግማሽ አመት ተመራቂ ተማሪዎችን ምርቃት በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጅስትራር በቀረበለት መሰረት፣ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በክረምት መርሐ ግብሮች በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ፣ 354 ሴት፣ 633 ወንድ፣ በድምሩ 9 መቶ 87 እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ለምረቃ ብቁ መሆናቸውን መርምሮ አፅድቋል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ነገ መጋቢት 13/2018ዓ.ም በሰመራ ከተማ በሚገኘው ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ አዳራሽ፣ ጠዋት ከ 2 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃል::

በተጨማሪም ሴኔቱ 18 የተግባር ሳይንስ ትምህርት ፕሮግራሞችን ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን፣ ፕሮግራሞቹ ለሴኔት የቀረቡት የተግባር ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ክለሳቸው በውስጥ እና የውጭ ባለሙያዎች ሲገመገሙ የቆዩና ሀገአቀፍ እና አለም አቀፍ የምዘና መስፈርት ተከልሰው የተጠናቀቁ፣ ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላታቸው ተረጋግጦ እንደሆነ ተገልጿል:

የፀደቁት 18 የተግባር ሳይንስ ትምህርት ፕሮግራሞች Applied Science curriculum፣ ከ3 ኮሌጆች እና ከ2 የትኩረት መስክ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ መሆናቸው ተመላክቷል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *