
አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት ከመጋቢት 01 እስከ ሚያዚያ 03/2018 ዓ.ም ክንውኖች
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ የሚካሄደው የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት አካል የሆነው፣ የ2018 ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃ-ግብር፣ከመጋቢት 01 እስከ ሚያዚያ 03/2018 ዓ.ም የተለያዩ ክንውኖች ተካሂደዋል፡፡


“የጤና ቀን” ከሰዕት በኋላ በተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምናና ጤና አጠባበቅ የግንዛቤ ስራዎች ተከናውኗል:: የእንስሳት ህክምና አገልግሎቱ በሰመራ ሎጊያ ከተማ አካባቢ ለሚገኙ እንስሳት የተሰጠ ሲሆን፣ አገልግሎቱን የእንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን እና የ6ኛ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ሰጥተውታል።
በተጨማሪም የህግ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች በአፋ/ብ/ክ/መ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚገኘው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የህግ አገልግሎት ማዕከል በመገኘት ለማህበረሰቡ ነፃ የህግ ማማከር እና የህግ ፅሁፍ አገልግሎቶችን ሰጥተዋል። ይህ መርሃ ግብር ነፃ የህግ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደጉ ተገልጿል።

የ2018ዓ.ም ዓመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት፣ “የቱሪዝም ቀን” የተለያዩ መርሃግብሮችን አካሂዷል:: “Visit Afar/አፋርን እንጎብኝ” በሚል መሪ ቃል ፣ ትኩረቱን በአፋር ክልል ድንቅ የተፈጥሮና የባህል መስህቦችንና መዳረሻዎችን፣ አገልግሎት ሰጪዎችን የሚያሳይ (Natural and Cultural Attractions and Hospitality Centers)፣ የፎቶ አውደ ርዕይ photo exhibition ቀርቧል::እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ዶ/ር ሬዶ የባህልና ሀገር በቀል ጥናቶች ማዕከል ሙዚየም የተጎበኘ ሲሆን፣ ለታዳጊዎች የአፋር ህዝብን፣ የታሪክ ድርሳናትና አሻራዎች፣የባህል እሴቶችና መገልገያዎች ጉብኝት እና ታሪክንና ባህልን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያ በአመራሮች ተሰጥቷል::በመርሃግብሩ ከቱሪዝም ቢሮ፣ ከሆቴል አገልግሎት ሰጪዎች፣ከት/ቤቶች የተጋበዙ እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣መምህራንና የቱሪዝም ተማሪዎች ተሳትፈውበታል።





