“ማህበራዊ ትስስራችን ለአብሮነታችን” በሚል ሀገር አቀፍ መድረክ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል::

“ማህበራዊ ትስስራችን ለአብሮነታችን” በሚል ሀገር አቀፍ መድረክ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሐምሌ_14 /2017

“ማህበራዊ ትስስራችን ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል::

“ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪና ማህበረሰብን ማቆራኘት ሲችሉ ኢትዮጵያ ታተርፋለች” ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ተናግረዋል::

የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክትን ልምድ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወስደው እንድተገብሩት ከስምምነት ላይ ተደርሷል::

samara family project

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ከሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ ዶ/ር ከይረድን ተዘራ ጋር የቤተሰብ ፕሮጀቱን ለማስቀጠል ያለመ ስምምነት ተፈራርመዋል::

በተመሳሳይ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት አመት በፊት ከየካቲት 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ የቤተሰብ ፕሮጀክት እየተገበረው የቆየ መሆኑ በመድረኩ ተነስቶ፣ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ አድናቆት እና እውቅናን ያገኘ ዩኒቨርሲቲ ሆኗል::

ዶ/ር መሀመድ በበኩላቸው የሰመራ ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክትን በአድስ ተነሳሽነት አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉት ገልጸዋል::

በመድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስተር አቶ መሀመድ እንድሪስ፣ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስተር ዲኤታ ዶ/ር ከይረድን ተዘራ፣በርካታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና የአማራ ክልል እና የጎንደር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *