
ማስታወቂያ
ለሠመራዩኒቨርሲቲ አንደኛአመት መደበኛተማሪዎች በሙሉ

ለሠመራዩኒቨርሲቲ አንደኛአመት መደበኛተማሪዎች በሙሉ
በ2016 የትምህርት ዘመን የ12 ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ሠመራ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና በ2016 በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 16 እስከ 17/2017 መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በተቋሙ ግቢ በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታካሂዱ እያሳሰብን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ
- የ8ኛክፍል ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- የ12ኛ ክፍል ሠርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- ስምንት 3*4 የሆነ ጉርድ ፎቶ-ግራፍ
- የግል መገልገያ ቁሳቁሶች ማለትም፡- አንሶላ፤የትራስ ልብስ፤የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትምጡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
በ2017 አዲስ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡