ሰመራ ዩኒቨርሲቲ_የካቲት 17/2018 ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የግማሽ አመት ሀገር አቀፍ የቅድመ ምረቃ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ጀምሯል።
ፈተናው ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች፣ ድጋሚ ለሚፈተኑ እንዲሁም ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚመጡ ተማሪዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የመውጫ ፈተናው ከየካቲት 17-27 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ካወጣው መርሐግብር ለማወቅ ተችሏል ።
