በስኬት_ተጠናቀቀ_Successfully_Concluded.

በስኬት_ተጠናቀቀ_Successfully_Concluded.

The 2nd Internationa Research Conference on “Leveraging Applied Knowledge for Transformative Change in Pastoral and Agro-Pastoral Communities” held from February 22-23/2025 has successfully concluded.

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ተኛው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ ተጠናቋል::

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2017 ዓ.ም-በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 2ተኛው አለምአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በስኬት ተጠናቋል:: ኮንፈረንሱ “ተግባራዊ እውቀትን ለአርብቶ አደር እና ከፊል-አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ለውጥ ጥቅም ላይ ማዋል” በሚል ርዕስ ነበር::

24 የምርምር ውጤቶች የቀረቡበት እና ከአውሮፓ -ጣሊያን፣ ከኤሲያ-ቻይና፣ከአፍሪካ-ኬንያ እንዲሁም ከካናዳ እና ከሀገራችን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን እና ከፌደራል እና ክልል መንግስት ተጋባዥ እንግዶችን ያሳተፈው 2ተኛው አለምአቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል::

በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ:በአፋር ክልል ያሉ ብዝሀ የተፈጥሮ ሀብቶችን በጥናትና ምርምር በመደገፍ ጥቅም ላይ ማዋል አስተዋፅኦው የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ሀገራዊ እና ነባራዊ ችግሮችን ለመፍታት መፍትሄ የሚሆኑ ጥናትና ምርምሮች መሰራታቸው የሚበረታታም እንደሆነ ገልጸዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ዑስማን በመዝጊያ ንግግራቸው እንደ አፋር ላሉ በረሃማና ከፊል በረሃማ አካባቢዎች ዘላቂ ልማት ለማምጣት የምሁራን ትጋት የጥናትና ምርምር ስራዎቻቸውን ወሳኝ በሆኑ ፖሊሲዎች ማካተት መቀጠል የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በኮንፈረንሱ የቀረቡ የቱሪዝም: የግብርና:የስነ-ምድር:ስነ-ህይወት እና የሰብአዊ መብት ጥናቶችን በተመለከተ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን ተመራማሪዎቹ ምላሽ በመስጠት ሁሉንም ያሳተፈ ኮንፈረንስ ተካሄዷል።

በኮንፍረንንሱ የቀረቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለበርካታ ማህበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መፍትሄ ጠቋሚ ምክረ-ሃሳቦች የተመላከቱበት ከመሆኑም በተጨማሪ አርብቶ አደሩንና ከፊል አርብቶ አደሩን ማህበረብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ” ባለ 10 ነጥብ የፖሊሲ ምክረሃሳብ/Policy Brief የተሰጠበት ነበር::

በኮንፍረንሱ መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሰመራ ሎጊያ አስተዳደር ከንቲባ፣ እና የሰመራ ዩዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል አቶ አብዱ ሙሳ እንደተናገሩት ‘የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ እና የክልሉን ፀጋ ተኮር የሆኑ ምርምሮችን በመስራት የጀመረው በጎ ጥረት መቀጠል እንዳለበት አመልክተው ከተለያዩ ቦታዎች የዩኒቨርሲቲውን ጥሪ አክብረው ለመጡ ተመራማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት በተደረገው 2ተኛው አለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ ለተሳተፉ ተጋባዥ እንግዶች እና ጥናት አቅራቢ ተመራማሪዎች የምስጋና የምስክት ወረቀት ሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *