በዩኒቨርሲቲው ለሶስት ቀናት የተሰጠው የአመራር ስልጠና ተጠናቋል::

በዩኒቨርሲቲው ለሶስት ቀናት የተሰጠው የአመራር ስልጠና ተጠናቋል::

ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች “The Twenty-First Century Instructional Leadership” በሚል ርዕስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተሰጠው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።

ይህ የስልጠና መድረክ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚፈልገውን፣ ዘመኑን የዋጀ የአስተዳደርና የአመራር ክህሎትን የሚያዳብሩ ቁምነገሮችን ለሁሉም የተቋሙ አመራሮች ለማስጨበጥ የተዘጋጀ መርሃ ግብር መሆኑ ተገልጿል::

ስልጠናው፣ በዘመናዊ የአመራር ጥበብ ንድፈ ሃሳብ እና በተግባራዊ አቀራረብ ተደግፎ የተሰጠ ሲሆን፣ የተቋምን ስትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካት ወሳ የሆኑ የማስተዳደርና የመምራት ክህሎቶችን የሚያስጨብጡ ጉዳዮችን የዳሰሰ፣ የካበተ ልምድ እና እውቀት ባላቸው፣ በፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ እና በዶ/ር አልማዝ ባራኪ የተሰጠ ነው::

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን እንደገለጹት ስልጠናው በዩኒቨርሲቲው ያለውን የአስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል፣በመጪው አመት የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካት የሚያግዝ ስንቅ ነው ብለዋል::

በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ በክብር እንግድነት ከተገኙት የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል እና የሰመራ ሎጊያ ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ ጋር በመሆን ሰልጣኞችን አመስግነው፣ለአሰልጣኞች ሽልማት አበርክተዋል ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *