
በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የትውውቅ እና የውይይት ፕሮግራም ተካሄደ::
ሚያዚያ 28/2017ዓ.ም -ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የዩኒቨርሲቲያቸውን የትምህርት፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራሞች የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ፣መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት የትውውቅ እና የውይይት መርሃግብር ተካሂዷል::
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት ኮሌኔል ሰለሞን ባኔ ስለ መከላከያ ቁልፍ ተልዕኮዎች አብራርተው በተለይ አሁን ላይ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ላይ መድረሱ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሚናው የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል።

ሻለቃ ዶ/ር በተለይ ተካ በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ስለመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታ ጀምሮ አሁን እስካለበት ቁመና አጠቃላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ስላሉት የተለያዩ ዕድሎችም ገለፃ አድርገዋል።
የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተማሪዎች የተነሱ ሲሆን ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው ባሉት ፕሮግራሞች ተማሪዎች በምርጫቸው ገብተው መማር እንደሚችሉበት እድል ክፍት እንዳደረገ አብራርተዋል።
መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ