
አመታዊው ተቋምን ከመሀል ሆኖ መምራት (Leading from the Middle)ፕሮግራም ተጀመረ።

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ የካቲት_24/2018-የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን መካከለኛ አመራሮችን ለማነቃቃት እና ተቋማዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር “ተቋምን ከመሀል ሆኖ መምራት (Leading from the Middle)” ያስጀምሩት ከሶስት አመት በፊት ነበር::

ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ የተገኘበትን ይህን አፕሮች ዘንድሮም በማስቀጠል፣ በጥናት በተለዩ ሶስት የስራ ክፍሎች፣ ማለትም በመስክና የቤተ-ሙከራ አስተዳደር፣የስነ ምድር ትምህርት ቤት እና በቋንቋዎችና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ በቅደም ተከተል ትግበራ ጀምረዋል:::
የዛሬውን መርሃ-ግብር በመስክና የቤተ-ሙከራ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተደረገ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን ወደ ተግባር ዩኒቨርሲቲነት ሽግግር መሰረት ያደረጉ ሶስት ዋና ዋና አላማዎች ያሉት ሲሆን፣ የቤተ-ሙከራ ማዕከሎች ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ ምልከታ፣ የግብአት አያያዝ ግምገማ እና በማእከሎቹ የቁልፍ የስራ አፈጻጸም አመልካቾች (KPIs) አፈፃፀም፣ የተግባር ስርአተ ትምህርት ጥራት ላይ ያተኮር ውይይት እና ግምገማ በማድረግ፣ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማሟያ አቅጣጫ መስጠትን ያካተተ ነበር።

አጠቃላይ ሂደቶቹን የፕሬደዳንት ፅ/ቤት የድጋፍ እና ክትትል ቡድን እያስተባበረው የሚገኝ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናት የስነ ምድር ትምህርት ቤት እና የቋንቋዎችና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ እንደሚካሄድ ተገልጿል።