”የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” የሴቶች ቀን 50ኛ አመት ኢዩቤልዩ

”የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” የሴቶች ቀን 50ኛ አመት ኢዩቤልዩ

ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ህዝብግንኙነት_መጋቢት07_2018-በዛሬው እለት አለም አቀፉ የሴቶች ቀን March8 ”የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃግብሮች፣ የፌደራልና የክልል ሴት አመራሮች ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሴት ምሁራን ጋር በመሆን በደማቁ ተከብሮ ውሏል::

March8፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን፣ በዛሬው መድረክ የውይይት መነሻ የሚሆኑ ሁለት ሰነዶች ቀርበዋል::

የመጀመሪያው የውይይት መነሻ ፅሁፍ “የኢትዮጵያ ሴት ሙህራን ሚና ” በሚል ርዕስ፣የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሰራተኞች ማህበር ፕሬዚደንት በሆኑት መምህርት ሰአዳ ኑሩ የቀረበ ሲሆን፣ ሁለተኛው የውይይት መነሻ ሰነድ፣ “የ50 አመት የለውጥ ጉዞና ማርች 8” በሚል ርዕስ፣ የአፋር/ብ/ክ/መ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ ሀላፊ በሆኑት ወ/ሮ ነስሮ ኡዳ ቀርቧል::

በቀረቡት የውይይት መነሻ ሰነዶች ላይ የፖናል ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከዩኒቨርሲቲው የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች በፓናሊስትነት፣ እንዲሁም ከተሳፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን ጨምሮ ውጤታማ የፓናል ውይይት መደረጉ ተገልጿል::

በመድረኩ የስነ-ፅሁፍ ስራዎች (ግጥም፣መነባንብ) በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ተጋባዝዥ እንግዶች ቀርበው መድረኩን አድምቀውታል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *