
የትምህርት ሳምንት ማጠቃለያ-የ5ተኛ ቀን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብር ተከናውኗል::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ግንቦት01/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት 5ተኛ ቀኑን ይዟል::
የትምህርት ሳምንት “Empowering Minds, Enriching Communities!” በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም ኮሌጆች በተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ መምህራን በሰመራ እና ሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የትምህርት አገልግሎት ዛሬ ተጠናቋል::

በዛሬው የማጠቃለያ ፕሮግራም የጥያቄ እና መልስ ውድድር፣ የአጠናን ስልቶችን ፣ የስነ-ልቦና ምክሮችን ለተማሪዎች መስጠት ተችሏል::
በሰመራ እና ሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መካከል በተካሄደው የጥያቄ እና መልስ ውድድር፣ የሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአሸናፊነት አጠናቋል::
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ለሁለቱም ትምህርት ቤቶች 500 የማጣቀሻ መፅሀፍት በስጦታ አበርክቷል::
መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ