የንግድ እና ስራ ፈጠራ ክህሎት የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::

የንግድ እና ስራ ፈጠራ ክህሎት የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::

#ሰመራ ዩኒቨርሲቲ_ታህሳስ_18_2018ዓም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከጂ.አይ.ዜድ-የግል ዘርፍ ልማት፣GIZ-Private Sector Development in Ethiopia (PSD-E) ፣ እና አፋር ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የሚተገብሩት የወጣቶች የንግድና ስራ-ፈጠራ ክህሎት ፕሮጀክት የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ጀምሯል::

ለ አምስት ቀናት በሚሰጠው የንግድ ክህሎት ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና 20 የሚሆኑ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአፋር ክልላዊ መንግስት የሥራና እና ክህሎት ቢሮ እና ከአይሣኢታ አዳዳሌ ኮሌጅ ለተውጣጡ አሰልጣኞች እየተሰጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ይህ ፕሮጀክት ከጀርመን መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ በአፋር ክልል 10 ወረዳዎች ለሚገኙ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች፣ከ2ሺህ በላይ ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ፣ ወጣቶችን በጥቃቅን እና አነስተኛ የንግድ ስራ ዘርፍ ለማስገባት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በክልሉ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና የግል ዘርፉን ለማሳደግ፣ እንድሁም የክልሉን ብሎም የሀገርን የንግድ እና የሥራ ፈጠራ እድሎችን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተብራርቷል።

በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም አሊ እና በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራና እና ክህሎት ቢሮ የክህሎት ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሀስና መሀመድ ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *