
የጥሪ ማስታወቂያ-Call for Remedial Students
የጥሪ ማስታወቂያ
በ2018 ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ
በ2018 የትምህርት ዘመን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሪሚዲያል (Remedial) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 25 እስከ 26/2018 መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በተቋሙ ግቢ በአካል በመገኘት ምዝገባ እንዲታካሂዱ እያሳሰብን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ
- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- ስምንት 3*4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number)
- የግል መገልገያ ቁሳቁሶች ማለትም፡- አንሶላ፤የትራስ ልብስ አሟልታችሁ እንድትምጡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት