
የጥሪ ማስታወቂያ
ለሠመራ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ነባር መደበኛ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመግቢያ ቀን በ07/01/2018 ዓ.ም እንድሁም የመመዝገቢያ ጊዜ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም ሲሆን መስከረም 12/2018 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እየገለፅን፣
በ2017 በሪሜድያል ፕሮግራም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንድሁም በመጪው 2018 በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደ ፊት በሌላ ማስታወቂያ የምንገልጽ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ:-ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን!
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት