
#የጥሪ_ማስታወቂያ
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የ1ኛ አመት አዲስ ገቢ እና ነባር የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ
በ2018 የትምህርት ዘመን በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ አመት አዲስ ግቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነባር ሪሚዲያል (Remedial) ተማሪዎች የምዝግባ ቀን ከጥቅምት 19 እስከ 20/2018 መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በተቋሙ ግቢ በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታካሂዱ እያሳሰብን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ:
- የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- የ12ኛ ክፍል ሠርተፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
- ስምንት 3*4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
- ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ (National ID) እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር(Tin Number)
- የግል መገልገያ ቁሳቁሶች ማለትም፡- አንሶላ፤የትራስ ልብስ፤የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትምጡ እናሳስባለን፡፡
- #ማሳሰቢያ፡-
- ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን፤
- በ2018 አዲስ የተመደባችሁ/የምትመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደ ፊት በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- የሠመራ ዩኒቨርሲቲ
- ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት