
የ Road Accident Data Management System (RADMS)የስልጠና ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ፣ መጋቢት 11/2017ዓ.ም-
ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው በዘመናዊ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አዲስ የ RADMS ድጂታል መተግበሪያ ስልጠና የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄዷል::
በስልጠናው ከ55 በላይ የአፋር ክልል የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት እና የፖሊስ ኮሚሽን እና እንዲሁም ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ የአይሲቲ ፣ የስታስቲክስ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል::
የ Road Accident Data Management System (RADMS) መተግበሪያ የፌደራል የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ፣ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እና ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ያበለፀጉት በመላ ሀገሪቱ ወደ ስራ የገባ መተግበሪያ መሆኑ ተገልጿል ነው::

መተግበሪያው ከወረዳ፣ዞን እና ክልል በየደረጃው የሚላኩለትን የትራፊክ መረጃዎችን በማቀናጀት ወደ ማዕከል ለመላክ የሚያስችል: አደጋን የመከላከል ፣ አደጋዎች ሲፈጠሩ ፈጣን ምላሽ የመስጠት እና መረጃዎችን በዘመናዊ መልኩ የመሰነድ እንዲሁም ለጥናትና ምርምር አገልግሎት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል::
ፕሮግራሙ የወደፊት የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እና ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል::

መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ