የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መካሄድ ጀምሯል።

የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መካሄድ ጀምሯል።

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ27/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት በተለያዩ መርሃግብሮች ዛሬ ተጀምሯል::

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ዶ/ ር መሀመድ ኡስማን (የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት)፣ የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ሀሚድ ዱላ (በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአፋር ክልል ባህል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ)፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኙበት የተከፈተው የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በቅርቡ በድንገተኛ አደጋ በሞት ለተለየን ለወጣቱ የስፖርት ጋዜጠኛ ኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ) የህሊና ፀሎት ተደርጓል::

በተጨማሪም ኑር ሁሴን በስፖርቱ ዘርፍ በዩኒቨርሲቲው እግርኳስ ክለብ እና ለክልሉ ስፖርት እድገት ላበረከተው ጉልህ አስተዋጾ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ሜዳ በስሙ ተሰይሟል::

ዛሬ በAdmin እና በCDA-Health College መካከል የተደረገው ጨዋታ አምና ዋንጫ በወሰደው Admin 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል:: በዛሬ ከሰአት መርሃ ግብር በAcademic Admin እና College of Engineering and Technology መካከል ጨዋታው የሚቀጥል ይሆናል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *