
ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ተከስቶ ለነበረው የፍየል ወረርሽኝ ምላሽ መስጠቱን ገለፀ::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ/23/2017 ዓ/ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ: የዱብቲ ወረዳ ማህበረሰብ በፍየሎች ላይ ሰሞኑን ለተከሰተው ወረርሽኝ አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለዩኒቨርሲቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ከሚያዚያ 18 እስከ 21/2017 ዓ.ም የተንቀሳቃሽ ህክምና አገልግሎት መስጠቱ ተገልጿል::
ዩኒቨርሲቲው ጥያቄውን ተቀብሎ የሀኪሞች ቡድን በመላክ በጥናት ላይ የተመሰረተ ህክምና በሽዎች ለሚቆጠሩ ፍየሎች እና በጎች በዋድ ባዱራ፤ ቀበሌ 03 እና ሂናሌ ቀበሌዎች ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል።

የሀኪሞቹ ቡድን ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ በቦታው ሲደርሱ 3 ፍየሎች ሙተው 100 የሚሆኑት በከባዱ ታመው ተቅማጥ፣ሳል የአፍንጫ ፍሳሽ እና ሙቀት የሚታይባቸው ፍየሎች ማግኘታቸውንና ማከማቸውን እንድሁም የግንዛቤ ትምህርት መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ባለሙያዎቹ ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ገልፀው የሚከተሉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ለህብረተሰቡ አስተላልፈዋል::
* የህመም ምልክት ሲያዩ የታመሙትን ከጤናማዎቹ ለይቶ ማቆየት: በተናጥል መመገብ እና በቂ የውሃ መስጠት
* አዲስ የሚገቡ ፍየሎችን ከመንጋው ጋር ሳይቀላቀሉ ለሁለት ሳምንታት ለይቶ መከታተል
* እንስሳቱ የተለመዱ በሽታዎችን መከላከያ ክትባቶችን መውሰዳቸውን ማረጋገጥ
* የበሽታ ስርጭትን ለመቀነስ መጠለያዎችን እና የምግብ እና የውሀ ቦታዎችን አዘውትሮ ማጽዳት:ንፅህናውን መከታተል
* የተለዩ ክስተቶችን ሲያዩ በአፋጣኝ ለእንስሳት ህክምና ማእከል/ባለሙያ ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል::
መሀመድ አህመድ አበጋር
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ