
ዩኒቨርሲቲው በሚሌ ወረዳ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ሰጠ።
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ07_2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት (Mobile Veterinary Service) በሚሌ ወረዳ በተመረጡ ሶስት ቀበሌዎች ሠጥቷል።

ለአራት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው የህክምና አገልግሎት ከ1ሺ 400 በላይ እንስሳትን የ Parasitism, Systemic Infection and wound ማከም መቻሉን ከሀኪሞች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የበሽታ መከላከል የህክምና አገልግሎትን በሌሎች አካባቢዎችም ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ከብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር እየተደረገ መሆኑን የእንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ አሳውቋል።
