ዩኒቨርሲቲው በርዕደ መሬት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ::

ዩኒቨርሲቲው በርዕደ መሬት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥር 01/2018 ዓ.ም–ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በርዕደ መሬት  (በመሬትመንቀጥቀጥ) ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ  የበራህሌ እና የኮነባ ወረዳ ነዋሪዎች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ም/ፕሬዚደንት አቶ አደም አሊ፣ ለበራህሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አሊ ሁሴን  እና ለኮነባ ወረዳ  አስተዳደር  አቶ መሐመድ ያህያእንዲሁም ድጋፍ ለማሰባሰብ የተቋቋመው ኮሚቴ ባለበት አስረክቧል።

​የዩኒቨርሲቲው በክልሉ በተደጋጋሚ የተከሰተ ላለው የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስ  ባለሙያዎችን በመላክ ግንዛቤ  መፍጠር እና የጉዳት መጠኑን ጥናት በማድረግ፣ እንድሁም በግሉ እና ሌሎች ተቋማትን በማስተባበር ድጋፎችን በመስጠት ከማህበረሰቡ ጎን የቆመ  ተቋም መሆኑን በርክክቡ ወቅት አመራሮቹ አውስተዋል።

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *