ዳጉ ጆርናል Daagu International Journal of Basic and Applied Research ዳግም እውቅና አገኘ::

ዳጉ ጆርናል Daagu International Journal of Basic and Applied Research ዳግም እውቅና አገኘ::

#ሰመራዩኒቨርሲቲ_የህዝብግንኙነት_የካቲት_24_2018-የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎችን ጥራትና እይታ ለማሳደግ እና ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለመጨመር በዘረጋው የጆርናሎች ምዘናና እውቅና አሰጣጥ ስርዓት መሰረት፣ 14 ጆርናሎች ‘እውቅና’ እና 11 ጆርናሎች ‘ዳግም እውቅና’ ያገኙ በማለት፣ በድምሩ 25 የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎችን ዝርዝር የካቲት 24/2018 አሳውቋል::

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዳጉ ጆርናል Daagu International Journal of Basic and Applied Research (DIJBAR)፣ መስፈርቱን አሟልቶ በመገኘቱ “ዳግም እውቅና” ማግኘቱ ተገልጿል::

ዳጉ ጆርናል (DIJBAR) ላለፉት ሶስት ዓመታት እውቅና ተሰጥቶት ጥራት ያላቸውን የምርምር ስራወች ሲያትም የቆየ ሲሆን፣ ለ 7ተኛ ዙር እንደተካሄደ በተገለጸው በዘንድሮው የጆርናሎች ምዘና “ዳግም እውቅና” ማግኘቱ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን እና እይታን እንደሚጨምርለት ተጠቁሟል::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ዳጉ ጆርናል ለቀጣይ ሶስት ተከታታይ ዓመታት የሚቆይ ዳግም እውቅና በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ ጆርናሉን ለመጎብኘትና ፣ የምርምር ስራዎችን ለማሳተም ይህን ማስፈንጠሪያ https://dagujournal.org/index.php/dijbar መጠቀም እደሚቻል ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *