ቢሮው ለአፋር ታለንት አካደሚ 10 ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አደረገ::

ቢሮው ለአፋር ታለንት አካደሚ 10 ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አደረገ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለአፋር ታለንት አካደሚ ተማሪዎች መገልገያ 10 ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን እንዲሁም በ2016 የት/ት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው ተማሪ መሀመድ አካድር የላፕቶፕ ኮምፒውተር አበርክቷል።

ድጋፉን ያስረከቡት የቢሮው ኃላፊ አቶ አህመድ መሀመድ ቦዳያ ሲሆኑ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱራህማን ከድር: የአፋር ብ/ክ/መ ት/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን እና ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ ሙሳ አደም በተገኙበት ለአካዳሚው የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀቢብ መሀመድ እና ለአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሀንፈሬ አስረክበዋል::

በስነ ስርዓቱ ላይ አቶ አህመድ መሀመድ ቦዳያ ባስተላለፉት መልዕክት: ድጋፉ የመጀመሪያ እንደሆነ እና በቀጣይም አካዳሚውን እንደሚደግፉና በተለይም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ልዩ ሽልማት ቢሯቸው እንደሚያበረክት ገልጸዋል::

አቶ አህመድ በመጨረሻም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችን:የክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎችን እና የአካደሚውን ኮሚቴ እና ሰራተኞች: ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን በመቀበል የትምህርት ዘርፉን ከታች ለመደገፍ እና በእውቀትና በስነምግባር የታነፀ ተተኪ ትውልድ ለማፍራት እየሰሩት ያለውን ስራ አድንቀው አመስግነዋል::

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች:የክልሉ ት/ት ቢሮ ሀላፊዎች እና የአካደሚው የቴክኒክ ኮሚቴ አስተዳደር እንዲሁም ተማሪዎች የፋይናንስ ቢሮ ላደረገው ድጋፍ እና ማበረታቻ አመስግነዋል::

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!!!

✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ

For Updates Follow,Share,Comment and Like our Social media pages.

Facebook👉https://www.facebook.com/susamara2008/

Telegram👉https://t.me/SamaraUniversityEthiopia

YouTube👉https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA…

Website👉Www.su.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *