ዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ ስልጠና ሰጠ::

ዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ ስልጠና ሰጠ::

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የንብረት አስተዳደር ሂደቱን ቀልጣፋ:ተአማኒ እና ብክነትን የሚቀንስ የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ ወደ ስራ ማስገባቱን ተከትሎ በተቋሙ ለአራቱም ዘርፍ በየደረጃው ላሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ከጥር 26-28 2017ዓ.ም ድረስ የቆየ በንብረት አስተዳደር ስራ-አስፈጻሚ የተዘጋጀ ስልጠና ሰጥቷል::

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ የአሰራር ሂደቱን ቀልጣፋ እና ተአማኒ የሚያደርጉ 10 የሚሆኑ መተግበሪያዎችን በፋይናንስ:በግዥ: በብቃትና ሰው ሀብት: በሬጅስትራር: ፈተናዎች ማዕከል እንዲሁም በሌሎች ክፍሎች በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል::

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ የመማር ማስተማር ስራውንም ወደ ኢ-ለርኒንግ ለማስገባት ዘመናዊ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ አስገንብቶ:መምህራንን እና ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኝ ተቋም ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *