በዩኒቨርሲቲው የመምህራን ማህበር ጉባኤ እና አዲስ የስራ-አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሄዷል::

በዩኒቨርሲቲው የመምህራን ማህበር ጉባኤ እና አዲስ የስራ-አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሄዷል::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ጥር_29_2017ዓ.ም

በዛሬው እለት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ማህበር ጉባኤ እና አዲስ የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሄዷል::

በጉባኤ ላይ ዶ/ር ዩሀንስ በንቲ የኢትዮጲያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት : ዶ/ር ፈቃዱ ዘለቀ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት: ዶ/ር መሀመድ ኡስማን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች: የኮሌጅና የት/ት ቤት ዲኖች:የት/ት ክፍል ሀላፊዎች እና የማህበሩ አባላት ተገኝተዋል::

በዚህ ምርጫ መሰረት

1. መሀመድ አሊ መሀመድ-የማህበሩ ፕሬዝዳንት

2. ዶ/ር ኢፋ ታደሰ ደበሌ-ም/ፕሬዝዳንት

3. ይባቤ ንጉሴ-ዋና ጸሃፊ

4. ነኢማ ሰይድ-ም/ዋና ጸሃፊ

5. አብዱልከሪም የህያ-ኦድተር

6. እልፍነሽ መዝገቡ-ፋይናንስ ሆነው በደሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት የአብላጫ ድምፅ በማግኘት ተመርጠው ቃለመሃላ ፈፅመዋል::

ይህ አዲስ አደረጃጀት በአጠቃላይ የተቋሙ መምህራንን መብት ማስከበር እና በተቋሙ ውስጥ በመማር ማስተማር ፣ በአስተዳደር ፣ በአቅም ማጎልበት ፣ በትምህርት ጥራት እና ሥነ ምግባር ጉዳዮችን በተደራጀ መልኩ ለመቅረጽ እና ለማንቀሳቀስ የሚያስችል አስተዳደራዊ ለውጥ እንደሚያምጣ አመራሮች እና አባላቱ አስተያየት ሰጥተዋል።

ተጋባዥ የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንቶቹ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን ቤት መስሪያ ከሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል አስተዳደር ተረክቦ ያጠረውን 200ሺ ካ.ሜ ቦታ ጎብኝተዋል። ከፍተኛ አመራሮቹ ለክልሉ እና ከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ላደረገው ቀና ትብብር የላቀ ምስጋና አቅርበዋል:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *