
ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር
ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት”በሚል ርዕስ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_የካቲት_11_ቀን 2017ዓ.ም
“ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር
ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት” በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ሰላም ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል::
የውይይት መነሻ ጥናታዊ ፅሑፍ በመምህር ሀይሌ ረዳ ቀርቦ በሰነዱ ላይ ጥያቄዎች ፣ አስተያየቶች እና ውይይት ተደርገዋል::
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳን ዶ/ር አብዱረህማን ከድር በመክፈቻ ንግግራቸው “እንደ ዜጋ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን እና ቀጠናዊ ትስስርን በሚገባ ተረድተን ሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማስፈን በሚያስፈልገው ሁሉ እንዲናበረክት ለማስገንዘብ የተዘጋጀ መድረክ ነው” ሲሉ ተናግረዋል::
በህ/ተ/ምክር ቤት የሰላም እና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የተከበሩ ወ/ሮ ውበቴ ታደገ ፣ “ዘላቂ ሰላም እና አገራዊ መረጋጋት ሊኖር የሚችለው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ ሲኖር ነው”።

እንደ አገር እና ዜጋ የጋራ የሆኑ ህልሞች፣ መገለጫዎች፣ ስጋቶች፣ ጥቅሞችና እሴቶች ያሉን ህዝቦች በመሆናችን የጋራ አረዳድን በማዳበር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በእያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ ማስረፅ አለብን” ብለዋል።
የተከበሩ አቶ ገዛሀኝ ጥላሁን ፣ በሰላም ሚኒስቴር የብሄራዊ መግባባት ዴስክ ሀላፊ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄዱ ያሉ መሰል ውይይቶች ለእርስበርስ እና ቀጠናዊ መግባባት ብሎም ለጋራ ጥቅሞቻችን መከበር ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል::
በመድረኩ ከሰላም ሚኒስቴር ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እና የካውንስል አባላት እንዲሁም መምህራን እና የተማሪ ተወካዮች ተሳትፈዋል::
