“በጀመርነው የ1 ሚሊዮን ተምር ልማት ትልቁን የምርምር እና የምርት ማዕከል እውን እናደርጋለን” ዶ/ር መሐመድ ኡስማን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለኢዜአ እንደገለጹት::

“በጀመርነው የ1 ሚሊዮን ተምር ልማት ትልቁን የምርምር እና የምርት ማዕከል እውን እናደርጋለን” ዶ/ር መሐመድ ኡስማን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለኢዜአ እንደገለጹት::

#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ_23_2017-“ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በአይሳኢታ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ማዕከል በ2ሺ 500 ሄክታር መሬት ላይ በቀጣይ 3 አመታት የእንስሳት መኖ ያመርታል: ከ8-10 ባለው አመት ውስጥ ደግሞ 1 ሚሊዮን ተምር በማልማት በሀገራችን ትልቁን የምርት እና የምርምር ማዕከል እውን እናደርጋለን” ሲሉ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሐመድ ኡስማን ትናንት ለኢዜአ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል::

ፕሬዚደንቱ እንደገለጹት የአይሳኢታ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ማዕከል ካፒታል ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምር እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረጉት ጥረቶችን በመደገፍ: በፆም ወቅት በሚሊዮን ዶላሮች ከውጪ የሚገባውን የቴምር ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚያስችል እና ለብዙዎች የስራ እድልን የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

አምና የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት የአዋሽን ወንዝ ከ6 ኪሜ ርቀት ላይ የመጥለፍ ስራው የተገባደደ ሲሆን: ሌሎች የግብርና መሰረተ ልማቶች ከ70 በመቶ በላይ ተከናውኗል::

የተምር ምርት በአፋር ክልል አይሳኢታና አፋምቦ ወረዳዎች በግለሰቦች እና በማህበራት ደረጃ ለብዙ አስርት አመታት እየተሰራበት ያለ ቢሆንም: በዘርፉ አንቱታን ያተረፉ አለም አቀፍ የምርምር ተቋማት እና ባለሀብቶች ጋር በመተባበር በምርምር እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የተምር ግብርናን እውን ለማድረግ ከተደረጉ ጥረቶች ውስጥ : የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በ2015 ዓ.ም የተባበሩት አረብ ኢመሬት አምባሳደር በኢትዮጵያ መሀ ሳሌም አል-መህዲ ጋር ውይይት አድርገው ነበር: በተጨማሪም ከሞሮኮ:ሳኡድ አረቢያ:ኩዌይት ኤምባሲዎች ጋር የተጀመሩ ግንኙነቶች አሉ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት አፋር ክልል ለበርካታ የምስራቅ አፍሪካ: ኤሲያ እና አውሮፓ ሀገራት ስትራቴጅካዊ ቅርበት ስላለው: ለወጪ እና ገቢ ምርት የገቢያ ትስስር አመቺ መሆኑ እና ከታወቁት የቴምር አምራች ሀገራት ጋር ተቀራራቢ የአየር ንብረት ያለው : እንዲሁም ሰፊ መሬት እና አመቱን በሙሉ የሚፈስ የውሀ ሀብት መገኛ መሆኑ : ፕሮጀክቱ ተስፋ የሚጣልበት አድርጎታል::

በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልየታ መሰረት የተግባር ተኮር ዩኒቨርሲቲ(University of Applied Science) ሆኖ መለየቱ እና የክልሉን ፀጋዎች ታሳቢ ያደረጉ የትኩረት መስኮች ማለትም ግብርና(የእፅዋት እና እንስሳት): ቱሪዝም እና ስነ-ምድር(ማዕድን) የተሰጡት በመሆኑ: የአይሳኢታ ግብርና ምርምር ማዕከል የተምር ፕሮጀክት የሀገራችንን የግብርና ታሪክ የሚቀይር እንደሚሆን ገልጸዋል::

ይህ ፕሮጀክት በ2018 መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ከማስተማሪያ እና ምርምር ማእከልነቱ በተጨማሪ ከሚያገኘው የእንስሳት መኖ ምርት እና በዋናው የተምር ምርት አማካኝነት ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት የሚሸጋገርበት ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል::

ቴምር በተፈጥሮ ብዙ ጥቅሞችን የተቸረው ተወዳጅ ምግብ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ::

የግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም የአፋር ክልል መንግስት የቴምር ምርትን ለማሳደግ በዩኒቨርሲቲው ብሎም በክሉ የነበሩና የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ትኩረት መስጠታቸው የሚመሰገን ነው::

በግብርና ሚኒስቴር እና በከሊፋ ዓለም ዓቀፍ የቴምር ልማትና ምርምር ተቋም የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና ከምርምር ተቋሙ የተውጣጣ ልኡክ በአፋር ክልል አይሳኢታና አፋምቦ ወረዳዎች ላይ እየተከናወነ ያለውን የቴምር ልማት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎች በተገኙበት የመስክ ምልከታ ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል።

✍️መሀመድ አህመድ አበጋር

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

✍️ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈጻሚ.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *