3ኛ ቀን-የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የተለያዩ ክንውኖችን አስተናግዷል።

3ኛ ቀን-የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የተለያዩ ክንውኖችን አስተናግዷል።

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት 3ኛ ቀን በተለያዩ መርሃግብሮች ማለትም በፅዳት ዘመቻ፣በጤና ምርመራ ፣እንስሳት ህክምና፣ነፃ የህግ አገልግሎት ክንውኖችን በማካሄድ ቀጥሏል:

በዛሬው የፅዳት እና የእፅዋት እንክብካቤ ቀን”ንፁህ እና ምቹ አካባቢ ለተሟላ ጤንነት” በሚል መሪ ሀሳብ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች በተገኙበት ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዋና በር ጀምሮ በዙሪያው ያሉ መንደሮችን የማፅዳት ስራ ተሰርቷል::

በማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር “በኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ)” እግርኳስ ሜዳ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ቀጥሏል::

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

✍️ መሀመድ አህመድ አበጋር

📸 ያሬድ አለሙ

የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *