
OneHealth-Free Mobile Veterinary & awareness Creation Service-ነፃ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎት እየተሰጠ ነው::
ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት የእንስሳት ጤና ሳምንት-3ኛ ቀን ፕሮግራሞች እንደቀጠሉ ናቸው። በዚህም ነፃ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ በሰመራ፣ሎጊያ እና ዱብቲ ዙሪያ አካባቢዎች ተካሂዷል::

ነፃ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ዩኒቨርሲቲው አመቱን በሙሉ በእቅድ የሚሰጠው አገልግሎት ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በስፋት ለተከታታይ ቀናት እያከናወነው ይገኛል::
በዚህም የእንስሳት ህክምናና ጤና ሳይንስና ኮሌጅ:የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕ/ፅ/ቤት እና የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ሚና የጎላ ነው::
መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ