
Health Screening-የደም ግፊት እና የስኳር ልኬት/ምርመራ ተከናውኗል::
ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት የጤና ሳምንት-3ኛ ቀን ፕሮግራሞች እንደቀጠሉ ናቸው። ትናንት በእጅጉ የተሳካ የደም ልገሳ ተካሂዷል::
በዛሬው የጤና ሳምንት አገልግሎት መርሃ ግብር ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ነፃ የጤና ምርመራ አገልግሎት ማለትም Blood Pressure and Blood Sugar Screening and Counciling ስራ ተከናውኗል::

በተጨማሪም የህክምናና ጤና ሳይንስና ኮሌጅ ባለሙያዎች በሰመራ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነፃ የጤና ትምህርት እና ምክር አገልግሎቶች በተለይ የግል እና የቡድን ጤና ፣ንፅህና፣አጠባበቅን የተመለከቱ ትምህርቶች ለተማሪዎች እየተሰጡ ነው::
መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ