
Journal of Afar-Af and Sociolinguistics ማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ግንቦት06/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ Journal of Afar-Af and Sociolinguistics የተባለ የምርምር ጆርናል ማስጀመሪያ መርሐግብር አካሂዷል::
ይህ ጆርናል በሁሉም የትምህርት መስክ፣ በዋናነት ግን በአፋርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮችን ለማሳተም ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ጆርናሉ ስለ አፋር ህዝብ ታሪክ ፣ባህል ፣ ወግ እና ቋንቋ የተሰሩ ብዝኃ መስክ(multi disciplinary) የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚታተሙበት በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ተነግሯል።
Journal of Afar-Af and Sociolinguistics ዓለም አቀፍ የምርምር ጆርናል ሊይዛቸው የሚገቡ ይዘቶችን ያካተተ መሆኑም ተመላክቷል።