የጥሪ ማስታወቂያ-Call for Remedial Students

የጥሪ ማስታወቂያ-Call for Remedial Students

የጥሪ ማስታወቂያ
በ2018 ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ
በ2018 የትምህርት ዘመን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሪሚዲያል (Remedial) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 25 እስከ 26/2018 መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በተቋሙ ግቢ በአካል በመገኘት ምዝገባ እንዲታካሂዱ እያሳሰብን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ

  1. የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
  2. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
  3. ስምንት 3*4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number)
  5. የግል መገልገያ ቁሳቁሶች ማለትም፡- አንሶላ፤የትራስ ልብስ አሟልታችሁ እንድትምጡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *