
በዩኒቨርሲቲው 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትዉልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር” በሚል መሪ ቃል ተከበረ::

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ህዳር 24/2018ዓም-ሠመራ ዩኒቨርሲቲ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትዉልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃም እየተከበረ ያለውን የጸረ-ሙስና ቀን በተቋም ደረጃ አክብሯል::

የንቅናቄ መድረኩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የካውንስል አባላት በተገኙበት፣ በፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ የድምፅ መልዕክት የቀረበ ሲሆን፣ በከፍተኛ አመራሮች የተመራ ውይይትም ተካሂዷል::
የዘንድሮዉ አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ያለመ ውይይት እና የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ያካሄዱ ከፍተኛ አመራሮች ሰነድ ለተቋሙ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ርክክብ በማድረግ፣ የንቅናቄ መድረኩ ተጠናቋል::


