ምክትል ዳይሬክተሩ ልዩ ሽልማት እና እውቅና ተበረከተላቸው።

ምክትል ዳይሬክተሩ ልዩ ሽልማት እና እውቅና ተበረከተላቸው።

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_መጋቢት_14 ቀን_2018-የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ለአቶ አቡበከር ካሳው (የዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራር ም/ዳይሬክተር) ልዩ ሽልማት እና እውቅና አበርክተዋል::

ለአስራ ስድስት ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ፣ በትጋት፣ በቅንነት እና በትህትና፣ ትምህርት ክፍል ኃላፊዎችን፣መምህራንን እና ተማሪዎችን፣ ያለምንም መስተጓጎል አገልግሎት በመስጠት እና የተቋሙን የትምህርት መረጃ በሚገባ በመሰነድ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተሰጠ ልዩ ሽልማት እና እውቅና እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

ልዩ ሽልማት እና እውቅና የተሰጠው ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የ2018ዓም 17ኛው ዙር የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ሲሆን፣ ምክትል ዳይሬክተሩ የተበረከተላቸውን የላፕቶፕ ሽልማት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን እና ከአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱርሃማን ከድር እጅ ተቀብለዋል።

እንደ አቶ አቡበከር ያሉ ታታሪና ሀገር ወዳድ ባለሙያዎች፣ ለወጣቱ ትውልድ፣ በተለይም ተመራቂዎች ወደ ሥራው ዓለም ሲገቡ ሀገራቸውን በቅንነትና በትጋት እንዲያገለግሉ ተምሳሌት እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

መሰል ሽልማት እና እውቅና መስጠት፣ ታማኝና ተግተው የሚሠሩ ሠራተኞችን ለማበረታታት፣ ለተቋማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የሚያሳይ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑ ተመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *