
ተመራቂ ተማሪ ላምሮት ጀግናው ሶሮታ በ2018 ዓ.ም ከተመረቁ የቅድመ-ምረቃ መርሃግብር ተማሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ዉጤት 3.89 በማምጣት ከወርቅ ሀብልን ጨምሮ፣ ድርብርብ ሽልማቶችን ወስዳለች።
ተማሪ ላምሮት በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል በእጅግ ከፍተኛ ማእረግ ከተሸለሙት አንዷ ነች፣ በኮሌጅ ደረጃ የሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች::
ከ17ኛው ዙር ተመራቂ ሴት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያመጣችውና የዓመቱን የወርቅ ሀብል ተሸላሚ ነች::

