Blog

Nov
28

ቢሮው ለአፋር ታለንት አካደሚ 10 ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አደረገ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለአፋር ታለንት አካደሚ ተማሪዎች መገልገያ 10 ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን እንዲሁም በ2016 የት/ት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው ተማሪ መሀመድ አካድር የላፕቶፕ ኮምፒውተር አበርክቷል። ድጋፉን ያስረከቡት የቢሮው ኃላፊ አቶ አህመድ መሀመድ ቦዳያ ሲሆኑ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱራህማን ከድር: የአፋር ብ/ክ/መ ት/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን እና ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ ሙሳ አደም በተገኙበት ለአካዳሚው የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀቢብ መሀመድ እና ለአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሀንፈሬ አስረክበዋል:: በስነ ስርዓቱ ላይ አቶ አህመድ መሀመድ ቦዳያ ባስተላለፉት መልዕክት: ድጋፉ የመጀመሪያ እንደሆነ እና በቀጣይም አካዳሚውን እንደሚደግፉና በተለይም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ልዩ ሽልማት ቢሯቸው እንደሚያበረክት ገልጸዋል:: አቶ አህመድ በመጨረሻም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችን:የክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎችን እና የአካደሚውን ኮሚቴ እና ሰራተኞች: ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን በመቀበል የትምህርት ዘርፉን ከታች ለመደገፍ እና በእውቀትና በስነምግባር የታነፀ ተተኪ ትውልድ ለማፍራት እየሰሩት ያለውን ስራ አድንቀው አመስግነዋል:: የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች:የክልሉ ት/ት ቢሮ ሀላፊዎች እና የአካደሚው የቴክኒክ ኮሚቴ አስተዳደር እንዲሁም ተማሪዎች የፋይናንስ ቢሮ ላደረገው ድጋፍ እና ማበረታቻ አመስግነዋል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!!! የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ For Updates Follow,Share,Comment and Like our Social media pages. Facebookhttps://www.facebook.com/susamara2008/ Telegramhttps://t.me/SamaraUniversityEthiopia YouTubehttps://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA… WebsiteWww.su.edu.et

DETAIL
Nov
28

The University held a Workshop on Earthquake Awareness Across Sectors in Afar Region.

#Samara_University_PRE-26 Nov, 2024 Today, a significant workshop focused on Earthquake Awareness Across Sectors took place at Samara University, organized by the Research and Technology Transfer Vice President Office in collaboration with the School of Earth Science. The event attended by members of the university community as well as representatives from various sectors from the regional government offices. The workshop featured a presentation by Samara University’s School of Geology, which highlighted recent studies, field observations, and community awareness campaigns conducted in the Awash Fentale area,where a series of frequent earthquakes happen over the past two months. The presentation was supported by relevant statistics drawn from national,regional and global earthquake experiences, underscoring the importance of understanding seismic activity. Participants engaged in fruitful discussions aimed at enhancing community awareness regarding earthquake risks and safety measures. The workshop served as a platform for sharing knowledge and fostering collaboration among local stakeholders, ultimately contributing to a more informed and prepared community in the face of natural disasters. #We_serve_the_community!!! Public Relations Executive For Updates Follow,Share,Comment and Like our Social media pages. Facebookhttps://www.facebook.com/susamara2008/ Telegramhttps://t.me/SamaraUniversityEthiopia YouTubehttps://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA… WebsiteWww.su.edu.et

DETAIL
Nov
28

PLRA Multi-Stakeholder Coordination Meeting Held at Samara University

Samara University PRE 26 Nov, 2024-The Partnership for Lowlands Resilience Activity (PLRA) convened a Multi-Stakeholder Coordination Platform Meeting at Samara University, from Nov 25-26/2024, bringing together various stakeholders, from Samara University, Afar regional government bureaus, woredas, kebeles and representatives from NGOs. The PLRA initiative aims to enhance coordination and communication among resilience stakeholders at multiple levels, improving the integration of interventions and reducing duplication of efforts. #We_serve_the_community!!! Public Relations Executive For Updates Follow,Share,Comment and Like our Social media pages. Facebookhttps://www.facebook.com/susamara2008/ Telegramhttps://t.me/SamaraUniversityEthiopia YouTubehttps://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA… WebsiteWww.su.edu.et

DETAIL
Nov
28

National Collaboration in Focus: Presidents of Assosa and Mizan-Tepi Universities Visit Samara University.

Samara University PR,25,Nov/2024. In a move aimed at enhancing national connectivity, Dr. Kemal Abdurehim, President of Assosa University, and Dr. Wako Geda, President of Mizan-Tepi University, have officially visited Samara University, accompanied by their respective teams. Upon their arrival, Dr. Mohammed Usman, President of Samara University, warmly welcomed the visiting dignitaries. He, along with his managment council, provided an in-depth briefing on the current status of Samara University, showcasing its progressive works and initiatives focused on transition to University of Applied Science,academic excellence and community engagement. This visit underscores the importance of inter-university collaboration in Ethiopia’s higher education landscape. Discussions are anticipated to revolve around potential partnerships, research collaborations, and the sharing of best practices to further enhance the educational experiences offered by the participating institutions. #We_serve_the_community!!! Public Relations Executive

DETAIL
Nov
28

ዩኒቨርሲቲው 1ኛ አመት መደበኛ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 16/2017ዓ.ም ሰመራ ዩኒቨርሲቲ: በ2016ዓ.ም የ12 ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት አምጥተው የተመደቡለትን አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና ባለፈው አመት በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል:: አሁን ወደ ግቢ በመግባት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 16 እና 17 መሆኑ ተገልጿል፡፡ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በማስታወቂያ እንደሚገለፅ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡ #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!!! የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ

DETAIL
Nov
28

የዩኒቨርሲቲው መምህራን የEntrepreneurship ስልጠና እየወሰዱ ነው::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ህዳር_16/2017ዓ.ም በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና በአፋር ክልል የስራ ፈጠራ ቢሮ በጋራ የሚያስተባብሩት እና የ የEntrepreneurship Development Institute (EDI) የሚሰጠው የስራ ፈጠራ(Entrepreneurship) ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው መምህራን መሰጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናውን በሁለት ዙር ከ90 በላይ ለሚሆኑ መምህራን ለመስጠት እንደታቀደ የተገለፀ ሲሆን:ዛሬ በተጀመረው እና 6 ቀን በሚቆየው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና 45 መምህራን እየተሳተፉ ነው:: ስልጠናውን የ የEntrepreneurship Development Institute (EDI) የካበተ ልምድ ባላቸው የራሱ ባለሙያዎች እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ መምህራን ይህን ስልጠና ሲያጠናቅቁ ማህበረሰቡን በሚጠቅም መልኩ: ወጣቶችን በማሰልጠን ወደ ስራ ፈጠራ እንዲገቡ እና በሙያ የታገዘ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል ያለመ ነው ::

DETAIL
Nov
28
Nov
22

የMakerspace አለም አቀፍ አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቀቀ::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ:ህዳር 12፣ 2017ዓ.ምበሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ከአፍሪካ እና አውሮፖ 9 ዩኒቨርሲቲዎችን በማሳተፍ የተካሄደው የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ሴቶች EtD-FaM Makerspace አለም አቀፍ አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቋል:: EtD-FaM Makerspace ፕሮጀክት ሴቶች የሙያ ስራ ሊማሩበት እና ሊሰሩበት የሚችሉበትን የመስሪያ ቦታዎች በተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማቋቋም እና ማጎልበት ሲሆን: ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ያሉ አስተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና መካከለኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መካከል ትስስርን ለመፍጠር ያለመ ነው። በአውደ ጥናት መክፈቻ እና መዝጊ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ፕሮጀክቱን ወደ አፕላይድ ሳይንስ በሽግግር ላይ ላሉ ዩኒቨርሲቲዎች በትክክለኛው ጊዜ የመጣ እውቀትን ከሚሰሩ እጆች ጋር የሚያገናኝ ሲሉ ገልጸውታል። አውደ ጥናቱ “Empowering Hands, Empowering Minds” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደ ሲሆን በታወቁ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ምሁራን 15 ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡበት እና Makerspace ልምድ ያካበቱ የዘርፉ ምሁራን የተመራ ተከታታይ ግንዛቤ ያላቸው ገለጻዎችና ውይይቶች ቀርበውበታል። በዚህ አውደ ጥናት በፕሮጀክቱ የታቀፉ 5 ዩኒቨርሲቲዎች (ሰመራ፣ ድሬዳዋ፣ ወሎ፣ አርሲ እና ወለጋ) ተወካዮች ከሀገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ የጅቡቲ፣የጣሊያ፣ የጀርመን እና ኦስትሪያ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች:እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር ዶ/ር ኤባ ሚጄና እና ዶ/ር ሰራዊት: የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈቃዱ ምትኩን ጨምሮ የፕሮጀክቱ አስተባባሪና ገምጋሚዎች ፕ/ር ዶ/ር-ኢንግ ቶማስ ቤንዝ: ዶ/ር ማርጋሬት ግፍሬር: ዶ/ር ማርዋ ቤን አሊ:ዶ/አሚና እና ተጋባዥ ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል:: ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት ለጀመረው ሽግግር የተዘጋጀ ፍኖተ ካርታ በአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አብዱረህማን ከድር የቀረበ ሲሆን ለሌሎች የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮው ይጠቅም ዘንድ በመፅሐፍ ታትሞ ለተሳታፊውች ተሰጥቷል። ይህ አውደ ጥናት ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጀመረውን የአለም አቀፋዊነት ጥረት ይበልጥ ያጠናከረ ከመሆኑም በላይ ከሀገር ውስጥ:እና ከሁለት አህጉር (ከአፍሪካ እና አውሮፓ) የትምህርት ተቋማት ጋር ለመተባበር እና እውቀትን ለመጋራት ተጨማሪ እድል የሰጠ መሆኑ ተገልጿል። በመጨረሻም ለጥናት አቅራቢ ምሁራን የምስክር ወረቀት እና ለውጪ እንግዶች የባህል ትውውቅን የሚገልፁ ባህላዊ አልባሳትን በመስጠት ተጠናቋል:: ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!!!✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

DETAIL