The Consortium of Ethiopian Public Universities (CEPU) has contributed 4,542,000 ETB in financial support for earthquake victims in Afar Regional State

The Consortium of Ethiopian Public Universities (CEPU) has contributed 4,542,000 ETB in financial support for earthquake victims in Afar Regional State

The Consortium of Ethiopian Public Universities (CEPU) has contributed 4,542,000 ETB in financial support for earthquake victims in Afar Regional State, facilitated by Samara University. Thank you to all member universities and leadership for your generous contributions.

የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ (መዩምመ) በአፋር ክልል በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ4.5ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ:የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ (መዩምመ) በአፋር ክልል በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ4.5ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_መጋቢት01/2017ዓ.ም-የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ (መዩምመ) በአፋር ክልል በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች 4 ሚሊዮን 542 ሺ ብር ድጋፍ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት አስረክቧል::

ድጋፉን ያስረከቡት የኮንሰርቲየሙ የቦርድ ም/ሰብሳቢ: የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል እና የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርሀነ መስቀል ጠና (ዶ/ር): የምክክር መድረኩ ቦርድ ሴክሬታሬያት ዋና ስራ አሰፈፃሚ ግርማ ወሰኔ (ዶ/ር) : የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኮንሰርቲየሙ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የድጋፉ አስተባባሪ መሀመድ ኡስማን (ዶ/ር) በጋራ በመሆን ለአፋ/ብ/ክ/መ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መሀመድ ሁሴን አስረክበዋል::

የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ (መዩምመ) 49 አባል ዩኒቨርሲቲዎች ያሉት ሲሆን: ከእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 23ቱ ከ4.5 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለወገኖች አድርገዋል::

የዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረኩ ምንም እንኳን የተቋቋመበት ዋና አላማ የተሻለ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን በዩኒቨርሲቲዎች ማረጋገጥ ቢሆንም ከተቋቋመበት 2003ዓ.ም ጀምሮ ለበርካታ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ተሳትፎ ማድረጉን ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ገልጸዋል::

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በበኩላቸው የኮንሰርቲየሙ ለሰጠው ፈጣን ሰብአዊ ድጋፍ አመስግነው:ሌሎች ተቋማትም የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ሲሉ አስተላልፈዋል::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ከጀመረበት መስከረም ወር ጀምሮ የበኩሉን የተለያዩ የቁሳቁስ እና የባለሙያ ድጋፍ ሲያደርስ የቆየ ሲሆን: በተጨማሪም ተቋማትን በማስተባበር ባሳለፍነው ወር የራያ ዩኒቨርሲቲ የቁሳቁስ ድጋፍ እንድሁም ዛሬ 23 ዩኒቨርሲቲዎች በኮንሰርቲየሙ በኩል 4.5ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረስ ተችሏል::

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

✍️ መሀመድ አህመድ አበጋር

📸 ያሬድ አለሙ

የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *