
በዩኒቨርሲቲው የቤተ-ሙከራ/የተግባር ትምህርት ሳምንት ተካሂዷል::
#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ_18 ቀን 2017 ዓ.ም-በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ሁሉንም ኮሌጆች እና ትምህርት ቤቶች ያሳተፈ የቤተ-ሙከራ እና የመስክ-ምልከታ የተግባር ትምህርት ሳምንት ተካሂዷል:: 
የተግባር ልምምድ ሳምንቱ አላማ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር እንዲሰሩ እድል መስጠት ሲሆን: ይህም የቡድን የንቅናቄ መንፈስን በማምጣት ከመደበኛው የቤተ-ሙከራ ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ በተማሪዎች እና በቤተ-ሙከራ ባለሙያዎች መካከል በትብብር መስራትን: መጠየቅን እና ደጋግሞ የመሞከር ባህልን መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል::

ይህ ተግባር በአመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ተቋማዊ ባህል ሆኖ የሚቀጥል በመሆኑ የዩኒቨርሲቲውን የተግባር ዩኒቨርሲቲነት ሂደት(Transition to University of Applied Sciences) ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ
በተለይ ኮሌጆች እና ት/ት ቤቶች: መምህራን:የቤተ ሙከራ ቴክኒካል ረዳቶች:ተማሪዎች ሁሉም በየደረጃው ለጉዳዩ የሚሰጠው ትኩረት እንዲጨምር ሚናው የጎላ ነው ተብሏል::