ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ::

ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ05_2017ዓ.ም ኢትዮ ቴሌኮም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ መደበኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ትናንት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል::

ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት 80 (ወንድ እና ሴት) ተማሪዎችን በመደገፍ በትምህርታቸው የያዙትን አላማና ፍላጎታቸውን እንዲያሳኩ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጾ: በቀጣይ በቁሳቁስም ድጋፉን አጠናክሮ የመቀጠል እቅድ እንዳለው አስታውቋል ። በመድረኩ ተማሪዎች የኢትዮ ቴሌኮምን አገልግሎቶች በብቃት ለመጠቀም በሚያስችሉ ክህሎቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል:: ይህም ለተማሪዎች አስፈላጊ ግብአቶችን ከማሟላት ባለፈ የኢትዮ ቴሌኮም አምባሳደር እንዲሆኑ የሚያነሳሳ የሚሰጣቸውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች የማስተዋወቅ ስራ ሰርቷል።

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ: ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች እያደረገው ላለው ድጋፍ ምስጋናውን እየገለፀ: ይህን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ተማሪዎችን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅም ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታን መፍጠር እንደሚቻል ያምናል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለአመታት በአጋርነት እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑም ተመላክቷል::

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

✍️ መሀመድ አህመድ አበጋር

📸 ያሬድ አለሙ

የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *