የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታላቅ የስነ-ፅሁፍ ምሽት አካሄዱ::

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታላቅ የስነ-ፅሁፍ ምሽት አካሄዱ::

በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን መምህራን:ሠራተኞች እና ተማሪዎች የታደሙበት መድረክ ‎ላይ ቲያትር ግጥም: ሞኖሎግ: ሙዚቃ:ዳንስ እና የጭውውት ትዕይንቶች ቀርበውበታል:: የዩኒቨርሲቲው “ድንቅ የተማሪዎች ክበብ” አባላት ዘወትር ቅዳሜ “አንድ ቀን ለራሴ “በሚል መርሀግብር የተለያዮ ፕሮግራሞችን በማቅረብ የሚታወቁ ሲሆን ከታዋቂ የስነ-ጥበብ ባለሙያ ጋር በመስራት ከ500 ሰው በላይ የተኘበት የጥበብ ምሽት ሲያዘጋጁ የዛሬው የመጀመሪያቸው ነው::

ተማሪዎቹ በስነ-ፅሁፍ እያዝናኑ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ሀሳቦችን በማንሳት መድረኩን ከማድመቅም ባለፈ የመማር ማስተማሩን እና የተማሪዎችን የግቢ ቆይታ አይረሴ የሚያደርጉ የጥበብ ስራዎችን በማቅረብ ቀልብ መግዛት መቻላቸውን የታዳሚው ቁጥር ምስክር ነው::

ምሽቱ ከስነ-ፅሁፍ ስራዎች በተጨማሪ:በሀገር አቀፉ የመላው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልኡክ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር እና በአዘጋጁ የአድስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት ተበርክቷል:: በተለያዩ ጊዜያት በተማሪዎች አቀባበል ላይ ተሳትፎ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል::በመጨረሻም የእለቱን የስነ-ፅሁፍ ምሽት ላዘጋጁት:ላስተባበሩት እና በትወና ላደመቁት ተማሪዎች ምስጋናና እውቅና በመስጠት ተጠናቋል::

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

✍️ መሀመድ አህመድ አበጋር

📸 ያሬድ አለሙ

የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *