
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “የምስለ-ችሎት ዉድድር” አካሄዱ።
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዝያ_03_2017 ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ህግ እና ስነ መንግስት ትምህርት ቤት: የህግ ተማሪዎች “የምስለ-ፍርድ ቤት ዉድድር” በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት አካሒደዋል።

የምስለ-ችሎት ውድድር በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ እንዲሁም በሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን:ተማሪዎች በፅንሰ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር የሚለማመዱበት መድረክ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ውድድሩን የዳኙት መምህራን ተናግረዋል::
ተወዳዳሪ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲያቸውን ወክለው በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የህግ ተማሪዎች ምስለ-ችሎት ውድድር ስለሚሳተፉ: የዛሬው ምስለ ችሎት ለቅድመ ዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ የተዘጋጀ መሆኑን ትምህርት ቤቱ ገልጿል።

መሀመድ አህመድ አበጋር
ያሬድ አለሙ
የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ