የግብርና ሙያዊ ድጋፍ-የ4ተኛ ቀን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብር ተከናውኗል::

የግብርና ሙያዊ ድጋፍ-የ4ተኛ ቀን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብር ተከናውኗል::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ30/2017ዓ.ም-የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የግብርና ቀን በህፀተ-ዝናብ አካባቢ ግብርና ኮሌጅ መምህራን ለዩኒቨርሲቲው የዱብቲ የፍራፍሬ ግብርና ማዕከል ሰራተኞችና የአካባቢው ማህበረሰብ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት አስችሏል::

የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንቱ ነገ 5ኛ ቀኑን የሚይዝ ሲሆን፣ላለፉት 4 ቀናቶች በሰመራ እና ሎጊያ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው የትምህርት አገልግሎት ማጠቃለያ ነገ ይካሄዳል:: በተጨማሪም የነፃ እንስሳት ህክምና፣ የህግ አገልግሎት መርሃግብሮች ማጠቃለያ ነገ ይካሄዳል::

ሳምንቱን በሙሉ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል ሲደረግ የነበረው የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር “በኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ)” እግርኳስ ሜዳ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፣የመረብ ኳስ፣የሩጫ እና ሌሎች ውድድሮችን አካቶ ቅዳሜ እለት ፍፃሜዉን የሚያገኝ ይሆናል::

#ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!

✍️ መሀመድ አህመድ አበጋር

📸 ያሬድ አለሙ

የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *