በክልሉ 10 ወረዳዎች ለ 500 ሰዎች ሲሰጥ የቆየው የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ::
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከGIZ-PSDE እና ከአፋር ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በ10 የክልሉ ወረዳዎች ለ250 የቢዝነስ ኢንተርፕራይዞች፣ 500 ሰልጣኞችን ያሳተፈ፣ ለ1 ወር ያክል በተለያዩ ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች ሲሰጥ የቆየው የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና የመጀመራ ዙር ማጠቃለያ በጭፍራ ከተማ ተካሂዷል:: በዚህ ስልጠና የተመረጡ ወረዳዎችና ከተማ አሰተዳደሮች አብዓላ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ፣ ሰመራ፣ ሎጊያ፣ ሚሌ፣ አይሳኢታ፣ በራህሌ እና ዱብቲ ሲሆኑ ከእያንዳንዱ ወረዳ 50 ሰልጣኞች ከ25 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተመረጡ ሲሆን፣ ከእያንዳንዳቸው ኢንተርፕራይዞች 2 ሰልጣኞችን በማሳተፍ ሁለገብ የንግድ ክህሎት ስልጠናውን ወስደዋል። ይህ ፕሮጀክት ከ GIZ፣ ከኔዘርላንድስ መንግሥት እና ከአውሮፓ ኅብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን ኢኮኖሚ ማንሰራራት ለማገዝ፣ በሥራ ፈጠራ፣ በፋይናንስ እውቀት እና በንግድ ስራ አስተዳደር ዙሪያ እየተተገበረ ያለ ነው። በተጨማሪም በቀጣይ እነዚህ ጥቃቅንና አነስተኛ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዞችን የሁለታኛ ዙር ስልጠና፣ የማማከር አገልግሎትና እና ከፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠርና በማገናኘት ከተቋማቱ ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ የሚያገኙበትን ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
SU Launches Training on Publication Ethics and Scientific Misconduct
Samara University PR | January 15, 2026-Samara University has launched a three-day training program on “Scholarly Publication and Scientific Misconduct” for its academic staff and researchers, aimed at strengthening research integrity and promoting ethical publishing practices. The training is expected to enhance participants’ understanding of international publication standards and equip them with practical skills to publish in reputable journals while avoiding scientific misconduct. It also emphasizes adherence to global research ethics to ensure the University’s scholarly output meets international expectations. The program is being delivered by senior researcher Kflay Gebrehiwot (PhD) and runs from January 15–17, 2026, with college and school deans and staff researchers from diverse academic disciplines in attendance. ሰመራ ዩኒቨርሲቲ “Publication and scientific Misconduct” (ህትመት እና የህትመት ሥነ ምግባር ) ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና እየሰጠ ነው:: ስልጠናው ተመራማሪዎች በአለም አቀፍ የምርምር ጆርናሎች ስራዎቻቸውን ማሳተም እንዲችሉ የሚያግዙ በህትመት ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤና ልምድ፣ የምርምርና የህትመት ሥነ ምግባር ህጎችን በማጎልበት፣ ጥራት ያለው ህትመት እንዲያበረክቱ፣ እንዲሁም፣ ዩኒቨርሲቲውን በአለም አቀፍ እይታ ውስጥ እንዲገባ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል። ስልጠናውን የኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ድኖች ከእያንዳንዱ የትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ መምህራን እየተሳተፉበት ነው።
The university delegation has successfully concluded a week-long international engagement tour in India.
Samara University’s Internationalization Team, led by Dr. Mohammed Usman, has successfully concluded a week-long educational and international engagement tour in India, culminating in official visits to Andhra University and Damodaram Sanjivayya National Law University (DSNLU). The tour resulted in productive discussions on joint academic and research initiatives, staff and student exchanges, scholarship opportunities, and training programs. These outcomes are expected to strengthen the University’s academic quality, research capacity, and global visibility, while advancing its commitment to South–South cooperation and sustained international partnerships.
ዩኒቨርሲቲው በርዕደ መሬት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ::
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥር 01/2018 ዓ.ም–ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በርዕደ መሬት (በመሬትመንቀጥቀጥ) ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የበራህሌ እና የኮነባ ወረዳ ነዋሪዎች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ም/ፕሬዚደንት አቶ አደም አሊ፣ ለበራህሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አሊ ሁሴን እና ለኮነባ ወረዳ አስተዳደር አቶ መሐመድ ያህያእንዲሁም ድጋፍ ለማሰባሰብ የተቋቋመው ኮሚቴ ባለበት አስረክቧል። የዩኒቨርሲቲው በክልሉ በተደጋጋሚ የተከሰተ ላለው የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስ ባለሙያዎችን በመላክ ግንዛቤ መፍጠር እና የጉዳት መጠኑን ጥናት በማድረግ፣ እንድሁም በግሉ እና ሌሎች ተቋማትን በማስተባበር ድጋፎችን በመስጠት ከማህበረሰቡ ጎን የቆመ ተቋም መሆኑን በርክክቡ ወቅት አመራሮቹ አውስተዋል። #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!
Samarâ jaamiqat Baaxoh Angoyyi Qawwalaylat biyaakitteh tan darifah Ayyuntah maaqiddi qokol Abte.
Samarâ jaamiqat asaakih ayrok January 9,2026-Samarâ jaamiqat Baaxoh Angoyyi Qawwalaylat biyaakitteeh buxaaxi kak finqitteh tan baraclê daqaarih ummattaa kee konnabí daqaarih ummattah 2 milyoonih birrik daga takke maaqiddaa kee eggerrâ mansoofah qokol Abte! Tama Qokol baracalê daqaarak naharsi saqal Gifta Qali Cuseen gitaak qokol koobaahissa makaadol tabsaanih taama tekke! Tonnaah kaadu konnabí daqaarih caddol yekkeh yan qokol, daqaarak naharsí Saqalah yan Gifta Macammad Yacya gabal tabsaanam tekke. Jaamiqat Awlisak A qokol tabseh Yan, Kusaq kee teknolojî tabaatabsak C/Prezxidantih yan Gifta Qali Adam elle qaddooseh yaninnal, Samarâ jaamiqat rakaakay caddol dibuh tan jaamiqat kinnuk, yan taqabih fidinaantee kee baaxô xexxar net haa waado ane mawayta immay, qakuu kee kulsal inkih Ayyunti xaqut nanno yaanam iyyeeh, tonnaah Jaamiqat abta qokol ixxigaa kee teknolojih qokolul akulsuyuk gexam qaddoose!! #Ummatta_ayfoofenno!!
ተማሪዎች የገና በዓልን በደማቅ ድባብ እያከበሩ ነው::
የ2018ዓ.ም የገና በአል በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል:: በድጋሜ መልካም በአል!!
ተማሪዎች የገና በዓልን በደማቅ ድባብ እያከበሩ ነው::
የ2018ዓ.ም የገና በአል በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል:: በድጋሜ መልካም በአል!!