Uncategorized

Mar
05

ዳጉ ጆርናል Daagu International Journal of Basic and Applied Research ዳግም እውቅና አገኘ::

#ሰመራዩኒቨርሲቲ_የህዝብግንኙነት_የካቲት_24_2018-የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎችን ጥራትና እይታ ለማሳደግ እና ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለመጨመር በዘረጋው የጆርናሎች ምዘናና እውቅና አሰጣጥ ስርዓት መሰረት፣ 14 ጆርናሎች ‘እውቅና’ እና 11 ጆርናሎች ‘ዳግም እውቅና’ ያገኙ በማለት፣ በድምሩ 25 የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎችን ዝርዝር የካቲት 24/2018 አሳውቋል:: የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዳጉ ጆርናል Daagu International Journal of Basic and Applied Research (DIJBAR)፣ መስፈርቱን አሟልቶ በመገኘቱ “ዳግም እውቅና” ማግኘቱ ተገልጿል:: ዳጉ ጆርናል (DIJBAR) ላለፉት ሶስት ዓመታት እውቅና ተሰጥቶት ጥራት ያላቸውን የምርምር ስራወች ሲያትም የቆየ ሲሆን፣ ለ 7ተኛ ዙር እንደተካሄደ በተገለጸው በዘንድሮው የጆርናሎች ምዘና “ዳግም እውቅና” ማግኘቱ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን እና እይታን እንደሚጨምርለት ተጠቁሟል:: ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ዳጉ ጆርናል ለቀጣይ ሶስት ተከታታይ ዓመታት የሚቆይ ዳግም እውቅና በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ ጆርናሉን ለመጎብኘትና ፣ የምርምር ስራዎችን ለማሳተም ይህን ማስፈንጠሪያ https://dagujournal.org/index.php/dijbar መጠቀም እደሚቻል ገልጿል።

DETAIL
Mar
05

ዩኒቨርሲቲው ለእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄደ::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_የካቲት_25/2018ዓ/ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የረመዳንን ፆም ምክኒያት በማድረግ ለእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች የኢፍጣር መርሃ ግብር በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ አካሂዷል። በዩኒቨርሲቲው መሰል ፕሮግራሞች መደረጋቸው በተቋሙ እና በተማሪዎች ዘንድ አብሮነትን: መተሳሰንብ እና ቤተሰባዊነትን እንደሚያጠናክሩ በማሰብ ነው::

DETAIL
Mar
04

ማስታወቂያ

ሁለተኛ ዙር የሁለተኛ ድግሪ ትምህርት ምዝገባ

DETAIL
Mar
04

ዩኒቨርሲቲው የዐብይ ጾምን አስመልክቶ ለተማሪዎቹ ልዩ የምሳ መርሃግብር አዘጋጀ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዐብይ ጾም ጹመው የዋሉ የኦቶዶክስ እምነት ተከታይ ተማሪዎችን የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል:: የምሳ ግብዣ ፕሮግራሙ የተካሄደው ተማሪዎች የእለቱን የፀሎት መርኃ ግብር አካሂደው ከተመለሱ በኋላ በዋናው የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ነው።

DETAIL
Mar
04

Call for Short Term Training

Online Registration link:-https://docs.google.com/…/1FAIpQLSeQUedE3Kb…/viewform…

DETAIL
Mar
03

አመታዊው ተቋምን ከመሀል ሆኖ መምራት (Leading from the Middle)ፕሮግራም ተጀመረ።

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ የካቲት_24/2018-የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን መካከለኛ አመራሮችን ለማነቃቃት እና ተቋማዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር “ተቋምን ከመሀል ሆኖ መምራት (Leading from the Middle)” ያስጀምሩት ከሶስት አመት በፊት ነበር:: ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ የተገኘበትን ይህን አፕሮች ዘንድሮም በማስቀጠል፣ በጥናት በተለዩ ሶስት የስራ ክፍሎች፣ ማለትም በመስክና የቤተ-ሙከራ አስተዳደር፣የስነ ምድር ትምህርት ቤት እና በቋንቋዎችና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ በቅደም ተከተል ትግበራ ጀምረዋል::: የዛሬውን መርሃ-ግብር በመስክና የቤተ-ሙከራ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተደረገ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን ወደ ተግባር ዩኒቨርሲቲነት ሽግግር መሰረት ያደረጉ ሶስት ዋና ዋና አላማዎች ያሉት ሲሆን፣ የቤተ-ሙከራ ማዕከሎች ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ ምልከታ፣ የግብአት አያያዝ ግምገማ እና በማእከሎቹ የቁልፍ የስራ አፈጻጸም አመልካቾች (KPIs) አፈፃፀም፣ የተግባር ስርአተ ትምህርት ጥራት ላይ ያተኮር ውይይት እና ግምገማ በማድረግ፣ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማሟያ አቅጣጫ መስጠትን ያካተተ ነበር። አጠቃላይ ሂደቶቹን የፕሬደዳንት ፅ/ቤት የድጋፍ እና ክትትል ቡድን እያስተባበረው የሚገኝ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናት የስነ ምድር ትምህርት ቤት እና የቋንቋዎችና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

DETAIL
Mar
02
Mar
01

ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

‎ጎረቤታሞቹ ሠመራ እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ በአፋር እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምናና የቅድመ መከላከል ክትባት (mobile Veterinary Service) አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። የአገልግሎቱ አላማ፣ በአዋሳኝ የዞን እና የወረዳ አካባቢዎች በርካታ የእንስሳት ሀብት የሚገኝበት፣ እንስሳቱ በገበያ፣ በግጦሽ እና ውሃ ለመጠጣት ዘወትር የሚገናኙበት በመሆኑ ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭነቱ፣ በተቋማቱ የጋራ ጥናት ተለይቶ፣ የቅድመ መከላከል ክትባት እና የጠቅላላ ህክምና አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ተብሏል:: በጭፍራ ወረዳ እየተሰጠ ባለው በአሁኑ የህክምናና ክትባት ዘመቻው ላይ ከሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ መምህራን እና ተማሪዎች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በጋራ አገልግሎት በመስጠት ላይ የቆዩ ሲሆን፣ ይህንኑ ለማስቀጠል በህዳር 2018 ዓ.ም ድጋሜ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ግንኙነታቸውን ማጠናከራቸው የሚታወስ ነው።

DETAIL