Blog

May
10
May
09

የትምህርት ሳምንት ማጠቃለያ-የ5ተኛ ቀን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብር ተከናውኗል::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ግንቦት01/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት 5ተኛ ቀኑን ይዟል:: የትምህርት ሳምንት “Empowering Minds, Enriching Communities!” በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም ኮሌጆች በተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ መምህራን በሰመራ እና ሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የትምህርት አገልግሎት ዛሬ ተጠናቋል:: በዛሬው የማጠቃለያ ፕሮግራም የጥያቄ እና መልስ ውድድር፣ የአጠናን ስልቶችን ፣ የስነ-ልቦና ምክሮችን ለተማሪዎች መስጠት ተችሏል:: በሰመራ እና ሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መካከል በተካሄደው የጥያቄ እና መልስ ውድድር፣ የሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአሸናፊነት አጠናቋል:: በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ለሁለቱም ትምህርት ቤቶች 500 የማጣቀሻ መፅሀፍት በስጦታ አበርክቷል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
May
09

የግብርና ሙያዊ ድጋፍ-የ4ተኛ ቀን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብር ተከናውኗል::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ30/2017ዓ.ም-የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የግብርና ቀን በህፀተ-ዝናብ አካባቢ ግብርና ኮሌጅ መምህራን ለዩኒቨርሲቲው የዱብቲ የፍራፍሬ ግብርና ማዕከል ሰራተኞችና የአካባቢው ማህበረሰብ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት አስችሏል:: የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንቱ ነገ 5ኛ ቀኑን የሚይዝ ሲሆን፣ላለፉት 4 ቀናቶች በሰመራ እና ሎጊያ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው የትምህርት አገልግሎት ማጠቃለያ ነገ ይካሄዳል:: በተጨማሪም የነፃ እንስሳት ህክምና፣ የህግ አገልግሎት መርሃግብሮች ማጠቃለያ ነገ ይካሄዳል:: ሳምንቱን በሙሉ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል ሲደረግ የነበረው የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር “በኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ)” እግርኳስ ሜዳ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፣የመረብ ኳስ፣የሩጫ እና ሌሎች ውድድሮችን አካቶ ቅዳሜ እለት ፍፃሜዉን የሚያገኝ ይሆናል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
May
08

OneHealth-Free Mobile Veterinary & awareness Creation Service-ነፃ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎት እየተሰጠ ነው::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት የእንስሳት ጤና ሳምንት-3ኛ ቀን ፕሮግራሞች እንደቀጠሉ ናቸው። በዚህም ነፃ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ በሰመራ፣ሎጊያ እና ዱብቲ ዙሪያ አካባቢዎች ተካሂዷል:: ነፃ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ዩኒቨርሲቲው አመቱን በሙሉ በእቅድ የሚሰጠው አገልግሎት ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በስፋት ለተከታታይ ቀናት እያከናወነው ይገኛል:: በዚህም የእንስሳት ህክምናና ጤና ሳይንስና ኮሌጅ:የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕ/ፅ/ቤት እና የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ሚና የጎላ ነው:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
May
08

3ኛ ቀን-የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የተለያዩ ክንውኖችን አስተናግዷል።

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት 3ኛ ቀን በተለያዩ መርሃግብሮች ማለትም በፅዳት ዘመቻ፣በጤና ምርመራ ፣እንስሳት ህክምና፣ነፃ የህግ አገልግሎት ክንውኖችን በማካሄድ ቀጥሏል: በዛሬው የፅዳት እና የእፅዋት እንክብካቤ ቀን”ንፁህ እና ምቹ አካባቢ ለተሟላ ጤንነት” በሚል መሪ ሀሳብ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች በተገኙበት ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዋና በር ጀምሮ በዙሪያው ያሉ መንደሮችን የማፅዳት ስራ ተሰርቷል:: በማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር “በኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ)” እግርኳስ ሜዳ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ቀጥሏል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
May
07

Health Screening-የደም ግፊት እና የስኳር ልኬት/ምርመራ ተከናውኗል::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት የጤና ሳምንት-3ኛ ቀን ፕሮግራሞች እንደቀጠሉ ናቸው። ትናንት በእጅጉ የተሳካ የደም ልገሳ ተካሂዷል:: በዛሬው የጤና ሳምንት አገልግሎት መርሃ ግብር ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ነፃ የጤና ምርመራ አገልግሎት ማለትም Blood Pressure and Blood Sugar Screening and Counciling ስራ ተከናውኗል:: በተጨማሪም የህክምናና ጤና ሳይንስና ኮሌጅ ባለሙያዎች በሰመራ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነፃ የጤና ትምህርት እና ምክር አገልግሎቶች በተለይ የግል እና የቡድን ጤና ፣ንፅህና፣አጠባበቅን የተመለከቱ ትምህርቶች ለተማሪዎች እየተሰጡ ነው:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
May
07

በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የትውውቅ እና የውይይት ፕሮግራም ተካሄደ::

ሚያዚያ 28/2017ዓ.ም -ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የዩኒቨርሲቲያቸውን የትምህርት፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራሞች የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ፣መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት የትውውቅ እና የውይይት መርሃግብር ተካሂዷል:: የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት ኮሌኔል ሰለሞን ባኔ ስለ መከላከያ ቁልፍ ተልዕኮዎች አብራርተው በተለይ አሁን ላይ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ላይ መድረሱ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሚናው የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል። ሻለቃ ዶ/ር በተለይ ተካ በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ስለመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታ ጀምሮ አሁን እስካለበት ቁመና አጠቃላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ስላሉት የተለያዩ ዕድሎችም ገለፃ አድርገዋል። የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተማሪዎች የተነሱ ሲሆን ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው ባሉት ፕሮግራሞች ተማሪዎች በምርጫቸው ገብተው መማር እንደሚችሉበት እድል ክፍት እንዳደረገ አብራርተዋል። #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
May
06

በዩኒቨርሲቲው አመታዊውን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት ሁለተኛ ቀን “የጤና ቀን” ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ ተካሂዷል።

#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ/2017-የ2017 አመታዊውን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት “የጤና ቀን” ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ተካሂዷል። በመርሃግብሩ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን፣ የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ መካከለኛ አመራሮች፣ ተማሪዎች በተገኙበት የደም ልገሳ ተካሂዷል:: የጤና አገልግሎቶች በተለያዩ የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃግብሮች በትምህርት ቤቶች ሳምንቱን በሙሉ እንደንሚካሄድ ተገልጿል:: የዚሁ የጤና ቀን አካል የሆነው ነፃ የእንስሳት ህክምና እና ጤና አጠባበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል::

DETAIL