Blog

Apr
14
Apr
14

ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ05_2017ዓ.ም ኢትዮ ቴሌኮም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ መደበኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ትናንት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል:: ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት 80 (ወንድ እና ሴት) ተማሪዎችን በመደገፍ በትምህርታቸው የያዙትን አላማና ፍላጎታቸውን እንዲያሳኩ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጾ: በቀጣይ በቁሳቁስም ድጋፉን አጠናክሮ የመቀጠል እቅድ እንዳለው አስታውቋል ። በመድረኩ ተማሪዎች የኢትዮ ቴሌኮምን አገልግሎቶች በብቃት ለመጠቀም በሚያስችሉ ክህሎቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል:: ይህም ለተማሪዎች አስፈላጊ ግብአቶችን ከማሟላት ባለፈ የኢትዮ ቴሌኮም አምባሳደር እንዲሆኑ የሚያነሳሳ የሚሰጣቸውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች የማስተዋወቅ ስራ ሰርቷል። ሠመራ ዩኒቨርሲቲ: ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች እያደረገው ላለው ድጋፍ ምስጋናውን እየገለፀ: ይህን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ተማሪዎችን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅም ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታን መፍጠር እንደሚቻል ያምናል። ኢትዮ ቴሌኮም ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለአመታት በአጋርነት እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑም ተመላክቷል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
Apr
14

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታላቅ የስነ-ፅሁፍ ምሽት አካሄዱ::

በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን መምህራን:ሠራተኞች እና ተማሪዎች የታደሙበት መድረክ ‎ላይ ቲያትር ግጥም: ሞኖሎግ: ሙዚቃ:ዳንስ እና የጭውውት ትዕይንቶች ቀርበውበታል:: የዩኒቨርሲቲው “ድንቅ የተማሪዎች ክበብ” አባላት ዘወትር ቅዳሜ “አንድ ቀን ለራሴ “በሚል መርሀግብር የተለያዮ ፕሮግራሞችን በማቅረብ የሚታወቁ ሲሆን ከታዋቂ የስነ-ጥበብ ባለሙያ ጋር በመስራት ከ500 ሰው በላይ የተኘበት የጥበብ ምሽት ሲያዘጋጁ የዛሬው የመጀመሪያቸው ነው:: ተማሪዎቹ በስነ-ፅሁፍ እያዝናኑ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ሀሳቦችን በማንሳት መድረኩን ከማድመቅም ባለፈ የመማር ማስተማሩን እና የተማሪዎችን የግቢ ቆይታ አይረሴ የሚያደርጉ የጥበብ ስራዎችን በማቅረብ ቀልብ መግዛት መቻላቸውን የታዳሚው ቁጥር ምስክር ነው:: ምሽቱ ከስነ-ፅሁፍ ስራዎች በተጨማሪ:በሀገር አቀፉ የመላው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልኡክ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር እና በአዘጋጁ የአድስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት ተበርክቷል:: በተለያዩ ጊዜያት በተማሪዎች አቀባበል ላይ ተሳትፎ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል::በመጨረሻም የእለቱን የስነ-ፅሁፍ ምሽት ላዘጋጁት:ላስተባበሩት እና በትወና ላደመቁት ተማሪዎች ምስጋናና እውቅና በመስጠት ተጠናቋል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
Apr
14

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “የምስለ-ችሎት ዉድድር” አካሄዱ።

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዝያ_03_2017 ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ህግ እና ስነ መንግስት ትምህርት ቤት: የህግ ተማሪዎች “የምስለ-ፍርድ ቤት ዉድድር” በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት አካሒደዋል። የምስለ-ችሎት ውድድር በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ እንዲሁም በሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን:ተማሪዎች በፅንሰ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር የሚለማመዱበት መድረክ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ውድድሩን የዳኙት መምህራን ተናግረዋል:: ተወዳዳሪ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲያቸውን ወክለው በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የህግ ተማሪዎች ምስለ-ችሎት ውድድር ስለሚሳተፉ: የዛሬው ምስለ ችሎት ለቅድመ ዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ የተዘጋጀ መሆኑን ትምህርት ቤቱ ገልጿል። #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
Apr
14

Samara University Hosts Workshop on Thematic Research.

#SamaraUniversity_PRE_9 April 2025—Samara University held a Capacity Development Workshop on “Thematic Research for Higher Education Institutions” to strengthen research among academic leaders and researchers. Topics included the concept and formats of thematic research, its integration with graduate studies, and aligning research budgets with institutional goals. The workshop emphasized the strategic role of thematic research in promoting academic excellence, collaboration, and national development goals. The initiative supports the university’s transition to a university of applied sciences by aligning research with industry and societal needs. The event attendees included the Vice President for Research and Technology Transfer, deans, directors, department heads, and senior researchers. #Weservethecommunity! PublicRelationsExecutive MohammedAhmedAbegar

DETAIL
Apr
14

Call for Business Idea and Innovation Projects

Samara University is excited to announce the launch of an Innovation and Business Idea Competition. This competition is open to all Samara University staff, students, and members of the university community. The University is also committed to fostering a vibrant entrepreneurial ecosystem, providing a range of entrepreneurship training programs, business incubation services, and comprehensive support for aspiring innovators and startup companies. Samara University’s Business and Technology Incubation Center is looking for dynamic innovators and business/technology incubates to transform their ideas into real business startup companies. This initiative aims to support startups that are ready to embark on growth and acceleration paths. We seek innovative business ideas that will enhance and strengthen the entrepreneurship and technology transfer ecosystem both at Samara University and within the surrounding community. #Who_is_Eligible_to_Apply? • Affiliation: Individuals must provide proof of their affiliation with Samara University (academic staff, administrative staff, or students). • Team Composition: Applicants may apply individually or as part of a team (maximum of three members). • Business Idea: Applicants should have a business idea or product that is ready for commercialization. • Commitment: Applicants must be willing to jointly commercialize their products upon agreement. • Innovative Business Idea: Individuals with business ideas that have the potential to develop into viable business ventures, with the support of training. • Engagement: Applicants must be motivated to actively engage in the business incubation process facilitated by the center. #Selection_Criteria • Feasibility and Scalability: The business idea or early-stage startup must be feasible and scalable. • Socio-Economic Impact: The idea should offer an innovative solution that has the potential to make a significant impact on the socio-economic development of the target community. • Impact on Productivity: The business should positively influence the productivity and profitability of existing businesses or ventures, ensuring long-term sustainability. • Uniqueness: The business idea/product must be unique and distinguishable from others in the market. • Commercialization Potential: Applicants should be capable of completing the commercialization process using resources available at Samara University’s labs, incubation center, or campus facilities. • Diversity: Special consideration will be given to applicants with disabilities (PWD) and female applicants. • Fulfillment of Eligibility Criteria • Quality of Responses to Application Questions #Benefit_Packages Selected innovators will receive: 1. Business Development Support Training 2. Mentorship and Coaching 3. Technical advisory 4. Networking with potential inverters 5. Seed Money Fund and more: Funds to be used for procuring tools, prototype development, and equipment purchases, in consultation with Samara University’s Business and Technology Incubation Center. #Important_Dates • Application Period: April 04, 2025 – April 25, 2025 • Announcement of Selected Business and Innovation Ideas: April 29, 2025 Note: Specific dates are subject to change based on circumstances. Any changes will be communicated to participants promptly. #How_to_Apply: • Submit your application via the [Google Form https://docs.google.com/…/1FAIpQLSc…/viewform…] during the open call period. • For inquiries, contact us at +251940026996 or email- iltt@su.edu.et Join us on an exciting journey to transform your startup idea into a successful real-world business!

DETAIL
Apr
14

ክክየምክር ቤት አባላቱ ለሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ ሰጡ::ክክ

#ሠመራዩኒቨርሲቲ_መጋቢት_27/2017 ዓ.ም_የአ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ ፣ ከሰው ሀብት ልማት ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ለዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄዷል:: ስልጠናው በሕይወት ክህሎት ዙርያ ማለትም በGoal Setting, Time Management and Designing Your Future ላይ ያተኮረ ሲሆን ሴት የምክር ቤት አመራሮች የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮአቸውን በዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ ዓመት እስከ ተመራቂዎች ድረስ ከ 500 ለሚልቁ ሴት ተማሪዎች አካፍለዋል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
Apr
14

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከመካከለኛ አመራሮች ጋር በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_መጋቢት_25/2017 ዓ.ም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በቁልፍ የአፈፃፀም ጉዳዮች ፣በመውጫ ፈተና ፣ የሰራተኞች የብቃት ምዘና እና ከመሀል ሆኖ መምራት ላይ ያተኮረ ውይይት ከመካከለኛ አመራሮች ጋር አድርገዋል:: ፕሬዚዳንቱ በመሩት በዚህ መድረክ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ በስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ እና በፕሬዝዳንቱ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተዘጋጁ የስራ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል:: መድረኩ በተነሱት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የዘርፎችና የክፍሎች ቁመና የተለየበት እና ድጋፍ ለሚሹት የክትትል እና ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩት ማበረታቻ የሚሆን የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጦ ተጠናቋል:: በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ ለዩኒቨርሲቲው ህክምና ትምህርት ቤት/School of Medicine ለተማሪዎች ተግባራዊ የህክምና ትምህርት መስጫ እየተሰናዳ ያለውን ልዩ Cadaver Dissection Room ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል:: #We_serve_the_community! Public Relations Executive

DETAIL